Connect with us

ከዶክተር አብይ ጎን በመቆም ከኦሮሞ ብልጽግና የሚሻለውን አብን ዶክተር አብይን ለመደገፍ በተጠራ ሰልፍ ማውገዝ፡፡

ከዶክተር አብይ ጎን በመቆም ከኦሮሞ ብልጽግና የሚሻለውን አብን ዶክተር አብይን ለመደገፍ በተጠራ ሰልፍ ማውገዝ፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ከዶክተር አብይ ጎን በመቆም ከኦሮሞ ብልጽግና የሚሻለውን አብን ዶክተር አብይን ለመደገፍ በተጠራ ሰልፍ ማውገዝ፡፡

ከዶክተር አብይ ጎን በመቆም ከኦሮሞ ብልጽግና የሚሻለውን አብን ዶክተር አብይን ለመደገፍ በተጠራ ሰልፍ ማውገዝ፡፡

ሳይወዳደር መሸነፍ የፈለገው ብልጽግናና የምርጫ ህጉን የጣሰው ስም ማጥፋት፤

 

(እሱባለው ካሳ)

ኦሮሞ ብልጽግና ትናንት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ ጠርቶ ነበር፤ ህዝቡ ከዶክተር አብይ ጎን መቆሙን አደባባይ ወጥቶ ሲገልጽም አይተናል፡፡ እርግጥ ነው ሰልፉ ውስጥ ተሰግስገው ከኦነግ ሸኔ ጎን መቆማቸውንም ያሳዩ ሰልፈኞችም ነበሩ፤ ለምሳሌ እወደዋለሁ ያሉትን ጠቅላይ የሚወዱትን አማካሪ በመርገም የሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ ቅኔው ሌላ እንደሆነ እንረዳለን፡፡

እርግጥ የድጋፍ ሰልፉ ፓርቲዎቹ የተስማሙባቸውን ሰነዶችና የፈረሟቸውን ስምምነቶች የጣሰ ነው፡፡ አደባባይ አብንን የማውገዝና የመስደብ አልፎም ስም የመስጠት ተግባር የራስን ፓርቲ ከማወደስም ሆነ ከመደገፍ ጋር ተዛምዶ የለውም፡፡ ገና ሳይወዳደር መሸነፍ የፈለገው ብልጽግና የምርጫ ህጉን ጥሷል፡፡ በዚህ ሀገር ቀድሞ የራስን ህግ ባለማክበር የጠራውን የማደፍረስ የመንግስት እኩይ ጠባይ ዳግም ሊታይበትም ይመስለኛል፡፡

ሰልፈኞቹን መሃል ተሰግስገው ነው ብንል እንኳን አንደኛ ሰልፉን የጠራው አካል ብሔር ተኮር ቅስቀሳን ማውገዝ ነበረበት፣ ሁለተኛ ባነሮችን ማዘጋጀት ይችል ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በራሱ አመራሮች ህገ ወጡን ተግባር አይደግመውም ነበር፡፡

ከንቲባን ያህል ነገር አደባባይ ላይ ገና ከወራት በኋላ ምርጫ በሚገጥሙት ህጋዊ ፓርቲ ላይ ስም ማጥፋት መዝመት ያስፈለጋቸው ምናልባትም ሰውዬው መሪዎቻቸው ከታሰሩባቸውና ከተጎዱባቸው ወገን ይሆኑ ይሆናል እንጂ ከዶክተር አብይ ጎን በመቆም ከኦሮሞ ብልጽግና የሚሻለውን አብን ዶክተር አብይን ለመደገፍ በተጠራ ሰልፍ ማውገዝ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ከምርጫ ጊዜው ማራዘም ሀሳብ ጀምሮ ሽግግር መንግስትን ጭምር በመኮነን ከለውጥ ሃይሉ ጎን የቆመው አብን ዓላማው ሀገር እንደነበረች አሳይቶ ተመስግኗል፡፡ ህወሃት ላይ የተወሰደውን የህግ ማስከበር ዘመቻም ቢሆን የኦሮሞ ብልጽግና ገና ጉዳዩ ሳይገባው የደገፈና ህዝብ አንቅቶ ለድል ያበቃ ፓርቲ ነው፡፡ ኦነግ ሸኔን ማባበል አንዱ አብንን ከኦሮሞ ብልጽግና ያቀያየመ ጉዳይ እንደሆነ ከየመግለጫዎቹ መለስ ብሎ ማየት ይቻላል፡፡ ከየብሔራችን አጥፊ አለና ከዚያኛውም አንድ እናካትት ዓይነት ድራማ የሚመስለው ለዚህ ነው፡፡

አብን ህጋዊ ፓርቲ ነው፡፡ ከብልጽግና ቀድሞ ምርጫ ምልክቱን የወሰደና በህግ አግባብ ተመዝግቦ እየሰራ ያለ ሆኖ ያለህግ በአደባባይ ሀገር አጥፊና አክራሪ ነው ብሎ በሚዲያ ጭምር ማወጅ ያሳፍራል፡፡

እርግጥ ነው፤ ሰልፉ ለአብን ጠቅሞታል፡፡ ሰው መንግስት የጠላውን መርምሮ የመቅረብ ባህል አለው፡፡ ከመንግስት የተጠጋን ያነውራል፡፡ ምናልባትም ሊጥሉት ያሰቡትን ፓርቲ ሳያውቁ ለድል ያበቁት ይሆናል፡፡ ለሁሉም ፓርቲዎችና ለሀገር የሚጠቅመው ግን የምርጫ ህጉንና የጋራ ስምምነታቸውን አክብሮ መስራት ነው፡፡ ( ከአዘጋጁ፡- ይህ ሐተታ የጸሐፊውን እንጂ የድሬቲዩብን የኤዲቶሪያል አቋም አያሳይም)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top