Connect with us

“ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ አሮጌ ብር መቀየር እንጂ መገበያየት አይቻልም”

"ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ አሮጌ ብር መቀየር እንጂ መገበያየት አይቻልም"
ሪፖርተር

ኢኮኖሚ

“ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ አሮጌ ብር መቀየር እንጂ መገበያየት አይቻልም”

“ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ አሮጌ ብር መቀየር እንጂ መገበያየት አይቻልም”

–         የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ

በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት የሚቻልበት የጊዜ ገደብ በሁለት ሳምንት እንዲያጥርና ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ መገበያየት እንደማይቻል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ ይፋ ባደረገው መረጃ፣ የብር ኖት ለውጡን ለማካሄድ የተሰጠው የሦስት ወራት ጊዜ ቢሆንም፣ አሮጌውን ብር የመለወጫ ጊዜ እንደተጠበቀ ሲሆን፣ በአሮጌው ብር መገበያየት የሚቻለው እስከ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ብቻ ነው፡፡

ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ አሮጌ ብር መቀየር እንጂ መገበያየት አይቻልም፡፡ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ አሮጌውን ብር በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየረ መሆኑን የሚያስታውሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ አሮውን ብር የመቀየር ሥራ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተወስኖ እስካሁን ባለው የመቀየሩ ሒደት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ሆኖም ግን አሮጌው ብር በአዲስ ብር የመቀየሪያው የመጨረሻ ቀን ታኅሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው፡፡ ከዚህ ቀን በኋላ አሮጌ ብር በባንኮች የማይቀየር እንደሆነም አስታውቋል፡፡

የብር ኖቶቹ መቀየሪያ ጊዜ የቀሩት ከሦስት ሳምንት ያነሰ ጊዜ በመሆኑ፣ በቀሪዎቹ ቀናት ያልተቀየረ ብር እንዲቀየርና ሒደቱን ለማፋጠን ሲባል ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ታኅሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ባሉት 15 ቀናት በአሮጌ ብር ግብይት መፈጸም የተከለከለ እንደሆነም አስታውቋል፡፡ ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ ግብይት በማከናወን የሚቻለው በአዲሱ ብር ብቻ እንደሚሆንና በእነዚሁ የመጨረሻዎቹ 15 ቀናት ማንኛውም ሰው አሮጌውን ብር ወደ ባንክ ሄዶ መቀየር እንጂ ሊገበያይበት የማይቻል መሆኑንም ማወቅ እንዳለበት ከባንኩ መረጃ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

(ምንጭ ፡- ሪፖርተር)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top