Connect with us

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉን የገንዘብ መጠን በድጋሚ ዝቅ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉን የገንዘብ መጠን በድጋሚ ዝቅ አደረገ
Ethiopian Reporter

ዜና

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉን የገንዘብ መጠን በድጋሚ ዝቅ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉን የገንዘብ መጠን በድጋሚ ዝቅ አደረገ

ባንኩ ከ ትናንትና የካቲት 29 ጀምሮ ይህንንና መሰል ጉዳዮችን የያዙ መመሪዎች ላይ ማሻሻያ ስለማድረጉና በማሻሻያዉም መሰረት ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉ የገንዘብ መጠን ለድርጅቶች ወደ 200 ሺ ብር እንዲሁም ለግለሰቦች ወደ 100 ሺ ብር ዝቅ እንዲል መደረጉን አሐዱ ቴሌቪዥን ከባንኩ ሃላፊዎች ሰምቷል፡፡

ባንኩ ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ገደብ የሚጥል መመሪያ ሲያወጣ በስድስት ወራት ዉስጥ ለ2ተኛ ጊዜ ሲሆን ከ ስድስት ወራት በፊት የወጣዉና እስካሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆዬዉ መመሪያ ከባንክ ዉጭ ሊኖር የሚችለዉ የገንዘብ መጠን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የባንኩ ምክትል ገዥና ችፍ ኢኮኖሚስት ፍቃዱ ደግፌ መጀመሪየዉኑም ተመሳሳይ ገደብ አለመጣል የትም ዓለም የሌለና አግባብነት ያልነበረዉ አሰራር ነዉ፤ ገንዘቡ የሀገር ሀብት ስለሆነ ባንክ ዉስጥ ገብቶ እየተንቀሳቀሰ ጥቅም ላይ መዋል አለበት ሲሉ የማሻሻያዉን አስፈላነትና ምክንያት ያሉትን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ የዳያስፖራ አካዉንት ባለቤቶች የገቢ ንግድ ላይ የሚሳተፉበት አካሄድም እንዲሁ ማሻሻያ እንደተደረገበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት  እነዚሁ ደንበኞች በአስመጭነት መሳተፍ የሚችሉት ባንኩ ቅዲሚያ ትኩረት እንዲያገኙ መርጫቸዋለሁ ባላቸዉ ዘርፎች ላይ የተወሰነ የዉጭምንዛሬ አቅርቦት እንደሚኖር ተገልጽዋል፡፡

እነዚህም ለፋብሪካ ምርቶች በግብዓትነት |የሚያገለግሉ  ጥሬ እቃዎች፣ መድሃኒቶች፣ እንዲሁም በተለዬ አስፈላጊ የተባሉ የምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ብቻ እንዲሆን ታስቦ መመሪዉን ማሻሻል እንዳስፈለገ የባንኩ ምክትል ገዥ አስረድተዋል፡፡(አሀዱ ቲቪ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top