Connect with us

ከህወሓት ጁንታ ጀኔራሎች አንዳንዶቹ በአዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንጻ አላቸው

ከህወሓት ጁንታ ጀኔራሎች አንዳንዶቹ በአዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንጻ አላቸው
Ethiopian press agency

ዜና

ከህወሓት ጁንታ ጀኔራሎች አንዳንዶቹ በአዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንጻ አላቸው

ከህወሓት ጁንታ ጀኔራሎች አንዳንዶቹ በአዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንጻ አላቸው

ህወሓት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሆነ ፖለቲካ በቤተሰብ ኔትዎርክ በመያዝ አገሪቷን ሲዘርፍ መኖሩን የትግራይ ክልል የሽግግር ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት እና የድርጅት ንቅናቄ ዘርፍ አባል አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ረዳ አስታወቁ። ቡድን ሲፈጠር ጀምሮ ከአንድ ቤተሰብ (ከስብሃት ነጋ ቤተሰብና አከባቢ) የወጣ መሆኑንም አመለከቱ።

አቶ ሊላይ ኃይለማርያም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዳመለከቱት፣ መሰሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን ሲፈጠር ጀምሮ ከአንድ ቤተሰብ (ከስብሃት ነጋ ቤተሰብና አካባቢ) የወጣ ነው ። 

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካ በዚህ የቤተሰብ ኔትዎርክ በመያዝ አገሪቷን ሲዘርፍ ኖሯል። በዚህም በቤተሰብና በአካባቢ ተደራጅቶ ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ሀብት ሲዘርፍ የቆየው የህወሓት ጁንታ ቡድን አዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንጻ ያላቸው ጄኔራሎችንም ፈጥሯል።

“ከስብሃት ነጋ ቤተሰብና አካባቢ የወጣው ይህ መሰሪ ቡድን ስልጣኑንም ኢኮኖሚውንም ለመቆጣጠር እንዲመቸው ሲል ከቤተ መንግስት እስከ ቤተ ክህነት ያለውን መዋቅር ሁሉ ተቆጣጥሯል። ለዚህ ደግሞ ስብሃት ነጋ መጀመሪያ አዲስ አበባ እንደገባ እና ስልጣን እንደያዘ አቡነ ጳውሎስን ከአሜሪካ አስመጥቶ ቤተ ክህነቱን አስያዘ። 

አቡነ ጳውሎስ ማለት ደግሞ የእነሱ ቤተሰብ ናቸው። አራት ኪሎ ቤተ መንግስቱን በመለስ አስያዙ፤ የመቀሌውን ቤተ መንግስት ደግሞ በቅዱሳን ነጋ ባል በአለቃ ፀጋዬ ነው የያዙት። እንዲህ አድርገው ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግስት ከተቆጣጠሩ በኋላ፤ ሁሉንም ነገር በኔትዎርክና በቤተብ ወደሚሰራ ሥርዓት አስገቡት” ብለዋል ።

ለምሳሌ፣ ቤተ ክህነት አንድ ህንጻ ቤተክርስቲያን ለማሳደስ ጨረታ ያወጣል። እናም አቡነ ጳውሎስ ያለምንም ጨረታ በአምስት ሚሊዮን ብር ጨረታውን ለኮሎኔል በላይ ይሰጡታል። ይሄ ሰውዬ ደግሞ ላይሰንስ የለውም፤ ኢንጂነርም አይደለም፤ ጡረታ የወጣ የደርግ ኮሎኔል እንደሆነ አመልክተዋል።

ሲኖዱሱም በአንድ ሚሊዮን የሚሰራ ስራ እንዴት በአምስት ሚሊዮን ይሰጣል በሚል ይሄንን አካሄድ ይቃወማል። የእሳቸውም ፀሃፊ የነበረውም በተመሳሳይ በመቃወሙ ጨረታው ይቆማል። ጨረታ ይውጣ ሲባል፣ 700 ሺህ፣ 800 ሺህ፣ አንድ ሚሊዮን የሚል ይወጣል። 

እሳቸው ደግሞ ይቆይ ብለው ያቆዩትና ከአንድ አራት ወር በኋላ በአምስት ሚሊዮን ብር ለእሱ ሰጥቼዋለሁ ብለው ያዛሉ። የዛኔም የሳቸው ፀሐፊ የነበረው በዚህ መልኩ አልሰራም ብሎ ስራውን ትቶ ወጥቷል። ከዛም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የስብሃት ነጋ ኔትዎርክ ሰዎች ናቸው ተሰብስበው እንዲገቡ የተደረገው እና የቤተ ክህነቱ የቢዝነስ መስመር በሙሉ ለእነሱ እንዲሰጥ ተደርጎ ሚሊየነር ሆነዋል ብለዋል።

እንደ አቶ ሊላይ ማብራሪያ፤ ከዚህ በተጓዳኝ የስዩም መስፍን፣ የስብሃት ነጋ እና የሌሎቹም ዘመዶቻቸው በኤርፖርት ይግቡ በጅቡቲ የጉምሩክ ታክስ ከፍለው አያውቁም። በአዲስ አበባ ተሸንሽኖ የተወሰደው መሬት ውስጥ አንዳቸውም በሊዝ ገዝተው አያውቁም፤ በሊዝ የገዙም ካሉ በሳንቲም ቤት ነው የሚገዙት። ይሄን ደግሞ ፋይሉን ከማዘጋጃ ቤት ወይም ከተማ ልማት ሊገኝ የሚችል ነው። 

እናም እነዚህ ሰዎች በሁሉም መስክ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረውት ቆይተዋል። ሌላው ቀርቶ ኮትሮባንድ ንግድ ከአብዲ ኢሌ ጋር ሆነው ሲሰሩ እንደነበር አመልክተዋል።(ኢፕድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top