Connect with us

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወደ ብሪታንያ በድጋሚ  ደብዳቤ ላኩ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወደ ብሪታንያ በድጋሚ ደብዳቤ ላኩ።
ኢኦተቤ ቴቪ

ነፃ ሃሳብ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወደ ብሪታንያ በድጋሚ  ደብዳቤ ላኩ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወደ ብሪታንያ በድጋሚ  ደብዳቤ ላኩ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እ.ኤ.አ 1868 በእንግሊዝ መንግሥት ከመቅደላ የትዘረፉ ቅርሶችን ታቦታትን ጨምሮ እንዲመልሱ የጻፉት ደብዳቤ በብሪቲሽ ሙዚየም ቦርድ በኩል በቀና መንገድ ታይቷል።

እንግሊዝ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከመቅደላ በ15 ዝሆኖች እና በ200 በቅሎዎች  ቅርሶችን ጭነው ዘርፈው ወስደዋል። ቅርሶቹ በተለያዩ የእንግሊዝ ሙዚየሞች እና ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ሲሆን በግለሰቦች እጅ የሚገኙትም በሚሊዮን ፓውንድ ይቸበቸባሉ::

 የመቅደላ ቅርሶች ከ400 በላይ ሲሆኑ ከቅርሶቹ መሀል ዘውድ፣ ታቦታት፣ ወደ 60 የሚጠጉ በብራና የተደጎሱ መንፈሳዊ መጽሐፍት፣ የአጼ ቴዎድሮስ የግል መጽሐፍ ቅዱስ እና የእቴጌ ምንትዋብ ነው ተበሎ የሚገመት ቀሚስ ይገኝበታል::

 ለወትሮው ከተለያዩ ሀገራት የተዘረፉ እና በብሪቲሽ ሙዚየም የሚገኙ የተዘረፉ ቅርሶችን ” የተማረኩ ” በሚል ስለ መመለስ ፈጽሞ ሀሳብ ያልነበራቸው የብሪቲሽ ሙዚየም የበላይ ኃላፊዎች ጉዳዩን እየተመለከቱት እንደሆነ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

 በገሀድ በማይታዩበት ሥፍራ በሙዚየሙ ውስጥ ከጎብኚዎች እይታ ዉጪ ተሰውረው የተቀመጡ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስያን ንዋያት ቅድሳት እንዲመለሱ ላለፉት ዓመታት በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና በመንግሥት በኩል ጥረት ሲደርግ ቆይቷል ::

 በዚህም ባለፉት ዓመታት ሁለት ታቦታትና ሌሎች ቅርሶች የተመለሱ ሲሆን ቀሪ ታቦታት እና ቅርሶች እንዲመለሱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሣት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  ለብሪቲሽ ሙዚየም ተደጋጋሚ ደብዳቤ ሲጽፉ ቆይተዋል::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤልን ስለጉዳዩ ለኢኦተቤ ቲቪ እንደገለጹት “በ ኮሺድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት መደበኛ ስብሰባው  ሲታጎል ቆይቶ በቅርቡ የተሰበሰበው በብርሪቲሽ ሙዚያም ያሉ ቅርሶችን በተመለከተ ወሳኝ የሆነው ጉባዔ የቅዱስነታቸውን ጥያቄ አዳምጧል፡፡

 ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ቅርሶቹን መመለስ የሚያስችሉ የሕግ ድንጋጌዎችን ማጤን መጀመሩ ቅርሶቹ ሊመለሱ እንደሚችሉ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች መኖራቸውን ያመለክታል ”ብለዋል።

 መ/ር ዳንኤል ቤተክርስቲያኗ በውጭ ግንኙነት መምሪያ በኩል ጉዳዮን እየተከታታለች እንደምትገኝም ገልጸዋል:

በመስከረም ወር ቅዱስነታቸው ለብሪቲሽ ሙዚያም በፃፉት ደብዳቤ ሙዚየሙን የሚያስተዳድረው አካል ከመቅደላ ተዘርፈው በእንግሊዝ ሙዚየም የሚገኙ ታቦታት እንዲመለሱ እንዲወስን በድጋሚ አሳስበዋል።

 ቅዱስነታቸው ሙዚየሙ በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባቸውን ቅዱሣት ንዋያት  በተለይም የቃል ኪዳኑን ታቦት ይመለሳሉ በሚል እየጠበቁ መሆናቸውን ገልጸው ፤ሙዚያሙ እነዚህን በዝርፊያ የሄዱ ታቦታት የመመለስ የሞራል ኃላፊነነት እንዳለበት አሳስበዋል።

 ቅዱስነታቸው በደብዳቤያቸው ታቦታቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በተለይም ለአማንያኑ ያላቸውን የተለየ ክብር እንዲሁም የምስጢራተ ቤተክርስቲያን መፈጸሚያ መሆናቸውን በማስረዳት የብሪቲሽ ሙዚየም እነዚህን ታቦታት በማይገባ ሥፍራ ማስቀመጡን አሣፋሪ ሲሉ ገልጸውታል ። ቅዱስነታቸው ጉዳዩ ትኩረትና ፈጣን ምላሽ የሚሻ  መሆኑንም አሰገንዝበዋል።

ታዋቂው ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ኦክቶበር 11 ዕትሙ ከ150 ዓመት በላይ ከእይታ ተሰውሮ የቆየው ታቦት ወደ ሀገሩ ሊመለስ መሆኑን ጠቁሞ ፤ ታቦት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ትልቅ መንፈሳዊ እሴት እንደሆነ በመግለጽ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ጥያቄው እንደቀረበ የሙዚየሙ አስተዳደርም ለመመለስ እያሰበ እንደሆነ ፍንጭ ማግኘቱን ገልጽዋል::

የብሪቲሽ ሙዚየም ታቦታቱ ለጎብኝዎች ዕይታ በማያውለው ጥናትና ምርምር በማይደረግበት  ፎቶግራፍ ማንሳት በማይቻልበት ሁኔታ አስቀምጦት እንደሚገኝ ዘጋርዲያን ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ታቦታቱ እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም ሙዚየሙ በሕጉ አንቀጽ 1963 መሠረት በሙዚየሙ የሚገኙ ቅርሶችን መመለስ እንደማይቻል እየገለጸ ጥያቄውን ውድቅ ሲያደርግ ቢቆይም ፤ ኢትዮጵያውያን በሕጉ ታቦታቱ ሊመለሱ የሚችሉበት የሕግ አግባብ መኖሩን በመጥቀስ ባደረጉት ቅስቀሳ ሙዚያሙ ታቦታቱን ሊመልስ እንዳሰበ አስነብቧል፡፡

ዘጋርዲያን አንዳንዶች ታቦታቱ ሊመለሱ አይገባም በሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡም ፤ ታቦታቱ ለሙዚየሙ የሚሰጡት ጥቅም እንደሌለ ለጥናት መዋል የማይችሉ በመሆኑ 11 የሚደርሱ ታቦታት ሊመለሱ እንደሚገባ የሚከራከሩም መኖራቸውን  በገጹ አስነብቧል፡

የብሪቲሽ ሙዚያም መቼ ታቦታቱን ለመመለስ እንዳሰበ ቁርጥ ያለ ውሣኔ አለማሳለፉን  ጋዜጣውን ዋቢ በማድረግ የዘገበው  E.O.T.C. TV ነው።

( ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም) 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top