የጠ/ሚኒስትር ዐብይ በዓለ ሲመት በህወሓቶች ዘንድ የፈጠረው ስሜት
(አሳዬ ደርቤ ~ ለድሬቲዩብ)
ጦርነት ቀስቅሰው አራት ኪሎ የመግባት እቅድ የነበራቸው የትሕነግ አመራሮች ጀኔሬተር ቀስቅሰው የጠ/ሚኒስትሩን በዓለ ሲመት በቲቪ ይመለከታሉ፡፡ ባንድ ወቅት የጌታቸው አሰፋ ተቋም “ሲፈልግ ተቆጣጣሪ፣ ሲያሻው አሸባሪ” በሚያደርጋው ደህንነቶች ቁጥጥር ስር የነበረውና የእነሱ ደስታ ማክበሪያ ስፍራ በነበረው አደባባይ ላይ… በአሸባሪነት የፈረጃቸው መንግሥት በዓለ ሲመቱን ሲያከብርበት እያዩ ‹‹ቴሌቪዥን እና ዘመን የማያሳየው የለም›› ይባባላሉ፡፡
እና ደግሞ ‹‹ዝግጅቱን በምንመለከትበት ቴሌቪዥን ፈንታ መስቀል አደባባይን የምንደበድብበት ድሮን ቢኖረን ኖሮ…›› እያሉ ይመኛሉ፡፡
በዚህ መሃከል ዶክተር ደጺ እራሱን እንደ ክልል ፕሬዝዳንት ቆጥሮ ‹‹እኛን ያላከተተ መንግሥት እንዴት ይመሠረታል?›› በማለት ሲጠይቅ ‹‹የአገር መሪዎች ሆነናል ብለን ከወሰንን በኋላ የክልል መሪዎችን ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ አይደለም›› ብሎ ጌታቸው ረዳ ከገሰጸው በኋላ ‹‹ይልቅ በዓለ ሲመቱን የሚያከብረው ጠቅላይ ሚኒስትር ከጎረቤት አገራት መሪዎች መሃከል እኛን ነጥሎ ሳይጠራን በመቅረቱ ዋጋ ልናስከፍለው ይገባል›› እያለ ይዝት ጀመር፡፡
በዛቻው መሃከልም በዓለ ሲመቱ ላይ የተገኙት የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ ‹‹ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር›› በሚል ምኞት ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ ‹‹በቀጣዩ ዘመቻ የጅቡቲን መስመር ብቻ ሳይሆን ጅቡቲ የተበላች አገርም ተቆጣጠረን ልናፈርሳት ይገባል›› በማለት ጌታቸው ረዳ አቋሙን ገለጸ፡፡
ይህ የጌቾ አቋም ግን፣ በሌሎች አመራሮች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ጂቡቲን በማውደም ሊቆም አልቻለም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የሌሎች አገራት መሪዎችም በዓለ ሲመቱ ላይ መገኘታቸው አልበቃ ብሏቸው ከህውሓት አቋም በተጻራሪ መልኩ “የኢትዮጵያን እናትነት” እና “የዘር ፖለቲካን ጉዳት” ለመናገር መድፈራቸው ሲሆን በዚህም ንግግራቸው የተበሳጩ የህወሓት አመራሮች ‹‹ይሄን አፍሪካ የተባለ ደካማ አሕጉር ሙሉ ለሙሉ እንደምስሰው እንዴ?›› የሚል ጥያቄ አንስተው ሲወያዩ ከቆዩ በኋላ ለግብጽ እናለሱዳን ሲሉ ምህረት አደረጉለት፡፡
ውይይታቸውን አቁመው ቲቪውን ሲመለከቱ መድረክ ላይ የቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ከአፍሪካ መሪዎች በማስቀጠል የአቶ ሃይለ ማሪያም ደሳለኝን እና የዶክተር ሙላቱ ተሾመን ሥም ሲጠሩ ማዳመጥ ቻሉ፡፡ ያን ጊዜም ለአፍታ ያክል በትዝታ ተጠልፈው ዶክተር ዐቢይን እንደ መድረክ መሪ በፈገግታ ሲመለከቷቸው ከቆዩ በኋላ የአገር መሪ መሆናቸው ትዝ ሲላቸው ከአፋቸው አስጠግተው የሚናገሩበት ማይክ የታንክ አፈሙዝ ሆኖ ደረታቸውን እንዲመታቸው ተመኙ፡፡
በጠ/ሚሩ ንግግር ውስጥም “ህወሓት ተብለን በክብር ሥማችን ባንጠራ እንኳን ‘ጁንታው’ ተብለን በሽብር ሥማችን መታወሳችን አይቀርም›› ብለው በጉጉት ሲጠባበቁ… ጠ/ሚሩ ምንም አይነት እውቅና ሳይሰጧቸው ንግግራቸውን መቋጨታቸው ከሚጠጡት ኢታኖል በላይ የሚያቃጥል ሆነባቸው፡፡ በዐቢይ የተወሰደባቸውን ብልጫም በሮማናት አደባባይ ጉዙፍ በዓለ ሲመት በማዘጋጀት ማካካስ ሲመኙ ፕሬዝዳንት እንጂ በጀት እንደሌላቸው ትዝ አላቸው፡፡
በዚህ መሃከል ታዲያ ኢቢሲን ሃክ ያደርግ ዘንድ የቀጠሩት ባለሙያ በሳተላይት ስልካቸው ደውሎ ገጹን ከመጥለፍ ባለፈም ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳንውል ሳናድር ከህወሓት ጋር እንደራደራለን ብለዋል›› ብሎ መጻፉን ሲነግራቸው በሞቅታ ስሜት እንበር ተጋዳላይን አስከፍተው ‹‹ጂጋኑ ጂጋኑ›› እያሉ ይጨፍሩ ጀመር፡፡ ሃከር ቀጥረው ተስፋቸውን የጻፉበትን ሚዲያ እንደ ጥንቱ አዲስ አበባ ገብተው የተቆጻጸሩት ይመስል በእራሳቸው የምኞት ቃላት እራሳቸውን ያስደስቱ ያዙ፡፡
ህወሓቶች ከጥንትም ጀምሮ መራር እውነትን ከመቀበል ይልቅ ከእራሳቸው ጣፋጭ ውሸት ከቻሉ ሌላውን ማታለል፣ ካልቻሉ እራሳቸውን መሸንገል የሚወዱ በመሆናቸው ‘ኢቢሲን ጠልፈን’ በማለት ፈንታ “መንግሥትን አስገድደን ወደ ድርድር አመጣነው” እያሉ ቺርስ መባባላቸውን ቀጠሉ፡፡
የሚገርመው ነገር ታዲያ በጠለፉት ገጽ ላይ “ምኞታችን ወጣ” ብለው መደሰታቸው ሳይሆን እንዲህ የሚል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው የእራሳቸውን ጥያቄ እራሳቸው ውድቅ ማድረጋቸው ነው፡፡
‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የእስር ማዘዣ ያወጣንባቸው የብልጽግና ባለሥልጣናት እጃቸውን ካልሰጡ በቀር ድርድር የሚባል ነገር አይታሰብም›› Lol