Connect with us

ዋናው ጥያቄ!

ዋናው ጥያቄ! (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ዋናው ጥያቄ!

ዋናው ጥያቄ!

(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የህዝቦች ትግል ባመጣው ለውጥ፣ ፓርቲዎ በአደራ በሰጥዎት የመሪነት ሀላፊነት፣ ፈታኙን የሽግግር ወቅት ችግር በእርስዎ፣ በህዝብዎና በሀገርዎ አቅም መጠን ተወጥተው፣  በሀገሪቱ ታሪክ የተሻለ የዲሞክራሲ ፋና የታየበት ምርጫ ተካሂዶ፣ በህዝብ ድምጽ የተመረጡ መሪ ለመሆን በመብቃትዎ በእንኳን ደስ አልዎት፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦችም በምርጫ አዲስ መንግስት ለመመስረት በመቻላችን እንኳን ደስ አለን፡፡

አይታ የማታውቀውን አዲስ መንግስት የመሰረተችው ሀገራችን፣ አይታ የማታውቀው ችግር ውስጥም ናት፡፡ ዛሬ የተመሰረተው መንግስት ስር ነቀል ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን  የሚጠይቅ ስራ ይጠብቀዋል፡፡ ሰላምን በሀገሪቱ በማስፈን የህወሀት አሸባሪ ጁንታዎች በቁጥጥር ስር መዋል አለባቸው፡፡ የአባይ ግድብ ተጠናቅቆ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት አስተማማኝ የሀይል መሰረት ላይ መቆም አለበት፡፡ 

የትምህርት ስርአታችን በገንዘብ በሚደግፉት ምእራባውያን አሽመድማጅ ፖሊሲ ሳይሆን፣ የህዝባችንን የእድገትና እራስን የመቻል ፍላጎት መሰረት አድርጎ መነደፍ አለበት፡፡ ሙስናን፣ አድሎንና የዜጎችን የመብት መገፈፍ እንዲወገድ/እንዲቀንስ የህግ የበላይነት መረጋገጥ አለበት፡፡ ከሁሉም በላይ ህገ-መንግስቱ የግለሰቦችን፣ የብሄረሰቦች/ህዝቦችን መብት በሚያረጋግጥና ሀገራዊ አንድነታችንን በሚያጸና መልክ መሻሻል አለበት፡፡ የምእራባውያን ጣልቃ ገብነትና ማእቀብ ከዚህ የከፋ ሊሆን ይችላል፤ እሱን ለመቋቋም ሀገርና ወገንን አስቀድሞ በኅብረት መቆም ያሻል፡፡. . . ወዘተ.

ባለንበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ሆነን ብዙ ልንቆይ አንችልም፡፡ ብዙ ችግሮች ውስጥ ነን፡፡ ብዙ ችግር ውስጥ ብንሆንም ተስፋ ይታያል፡፡ ከብዙ ችግሮቻችን መካከል የተወሰኑትን እንኳን ቀርፎ፣ የተስፋውን መንገድ ለመያዝ ብዙ ስራ ከተመሰረተው መንግስት ይጠበቃል፡፡

የምርጫው ስኬት ተስፋ ነው፡፡ በምርጫ መንግስት መመስረቱ ተስፋ ነው፡፡ ጠ/ሚንስትሩ እንዳሉት፣ ‹‹ዋናው ጥያቄ ተስፋውን እውን ለማድረግ ምን ያህል ቁርጠኞች ነን?›› ይህን ጥያቄ እያንዳንዱ ተመራጭ እራሱን መጠየቅ አለበት፡፡. . .  እያንዳንዱ ዜጋም እንዲሁ!

የአዲሱ መንግስት የስራ ዘመን ከማነቆ ችግሮቻችን ወጥተን፣ በተስፋ የእድገት ጎዳና ላይ በሁለት እግሮቻችን የምንቆምበት ይሆን ዘንድ ተስፋ አለኝ፡፡ ለጠ/ሚንስትር አብይ አህመድና ለአዲሱ መንግስታቸው በተግባራዊ ስኬት የደመቀ የስራ ዘመን እመኝላቸዋለሁ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top