Connect with us

“ሙስሊም አገራት በታሪክ ሊዘነጋ የማይችል የኢትዮጵያ ውለታ አለባቸው”

"ሙስሊም አገራት በእስልምና ኃይማኖት ታሪክ ሊዘነጋ የማይችል የኢትዮጵያ ውለታ አለባቸው"

ባህልና ታሪክ

“ሙስሊም አገራት በታሪክ ሊዘነጋ የማይችል የኢትዮጵያ ውለታ አለባቸው”

“ሙስሊም አገራት ሁሉ በእስልምና ኃይማኖት ታሪክ ኢትዮጵያ ላበረከተችው ጉልህ አስተዋፅኦ ሊዘነጋ የማይችል ውለታ አለባቸው” ሲሉ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ሸህ መሐመድ ሲራጅ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የዑለማ ምክር ቤት አባልና የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ሸህ መሐመድ ሲራጅ ከሌሎች የኃይማኖት አባቶች ጋር በመሆን ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ ኢዜአ ያነጋገራቸው ሸህ መሐመድ ሲራጅ በእስልምና ኃይማኖት ታሪክ ኢትዮጵያ የነበራትን አስተዋፅኦ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የነብዩ ሙሀመድን ሱሃባዎች ተቀብላ ያስተናገደች ታሪካዊ አገር መሆኗን ጠቅሰዋል። ለዚህም የዓለም ሙስሊም አገራት ሁሉ በእስልምና ኃይማኖት ታሪክ የኢትዮጵያን ጉልህ አስተዋፅኦ ሊዘነጉት አይችሉም፤ ትልቅ ውለታም አለባቸው ነው ያሉት።

በመሆኑም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታራምደውን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መርህ ሁሉም የሙስሊም አገራት ሊደግፉት ይገባል ብለዋል።

ጎረቤቶቻችን ውሃ እንዲያጡ እንደማንፈልገው ሁሉ እነሱም ኢትዮጵያ ጥቅም እንድታጣ፣ ኢትዮጵያዊያን እንዲጠሙና እንዲራቡ መመኘት ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ልዩነት በገዘንባቸውና በላባቸው እየገነቡት ያለው ግድብ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የግድቡ ግንባታም ማንኛውንም አገር የመጉዳት ዓላማ ያነገበ ሳይሆን በጨለማ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊንን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በተለይም የአረቡ ዓለም አገሮች ለኢትዮጵያ ዕድገትና ልማት መተባበር እንጂ ሳንካ መሆን አይገባቸውም፤ የኢትዮጵያን መብት መጠበቅ ግዴታም አለባቸው ነው ያሉት።

በሀበሻ ምድር ፍትሐዊ መንግሥት አለ ብለው ነብዩ ሙሐመድ ወደ ኢትዮጵያ የላኳቸው ሱሃባዎች መጠጊያ ያገኙት በታሪካዊቷ አገር ኢትዮጵያ መሆኑን ሸህ መሐመድ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ አድርጋ እንደምትሰራ ሁሉ ግብጽና ሱዳንም የትብብርና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን አላማ የዘው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

ምንጭ:- ኢዜአ

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top