Connect with us

እንዲህ ያለ ጡዘት በዘራችሁ አይድረስ!

እንዲህ ያለ ጡዘት በዘራችሁ አይድረስ!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

እንዲህ ያለ ጡዘት በዘራችሁ አይድረስ!

እንዲህ ያለ ጡዘት በዘራችሁ አይድረስ!

(መላኩ ብርሃኑ)

የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለስልጣን  በግል ትምህርት ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ላይ ያወጣውን መግለጫ ዛሬ አየሁት።

“ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና መዝገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ባለስልጣን ባወጣዉ የማስፈጸሚያ ማኑዋል መስረት መስራት እየተገባቸዉ ባለመፈጸም በርካታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ አድርገዋል፡፡” ይላል።

ማን ፈቅዶላቸው ይህንን እንዳደረጉማ ራሱ ያውቀዋል። የተወጋ አይረሳምና ባለስልጣኑ የተናገረውን ነገር ቃል በቃል እናስታውሰዋለን። 

ባለፈው ሃምሌ 23 ቀን 2013 ባወጣው መግለጫ ምን አለ?

“ተቋሙ ትኩረት የሚያደርግበት እና የሚወስነው የምዝገባ ክፍያን ከመገደብ ጋር በተገናኘ ብቻ ይሆናል።  የትምህርት መመዝገቢያ የገንዘብ መጠን ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈለገው ትምህርት ቤቶች ለመመዝገቢያ ክፍያ የሚጠይቁት ገንዘብ ከፍተኛ ስለነበረ ነው ።

ያ ስለሆነም የምዝገባ ክፍያው ከወርሃዊ የትምህርት ክፍያ ተመኑ 25 በመቶ ብቻ እንዲሆንና ከዚህ በላይ ጭማሪ እንዳይደረግበት ተወስኗል። ወርሃዊ ክፍያን በተመለከተ ተቋሙ ጣልቃ አይገባም።

ስምምነቱ በትምህርት ቤቶች እና በወላጆች መካከል ይሆናል። ጭማሪው ትምህርት ቤቶቹ በሚያስቀምጧቸው በቂ ምክንያች እና በወላጆች በመተማመን ይወሰናል” አለ። (ምንጭ አሃዱ ራዲዮ)

በዚህ መግለጫ የልብ ልብ የተሰማቸው ትምህርት ቤቶች እስከ 40 እና 50 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ወላጅን “ከፈለግክ አስተምር ካልፈለክ ልጅህን ውሰድ”  አሉ። እነሆ የቻለ ወላጅ አስመዝግቦ ፣ ያልቻለ የመንግስት ትምህርት ቤት አስገብቶ፣  ትምህርት ቤቱም የምዝገባ ገንዘቡን ሰብስቦና አካውንቱ አስገብቶ አሁን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ተጠናቅቋል። አለቀ !

ይህን ያየ ጋሽ ባለስልጣን ደግሞ ሆን ብሎ ከተኛበት ድንገት ተነሳና “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” አይነት ዘራፍ ጀመረ። አያገባኝም ባለ ልክ በአንድ ወሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ምን አለ?

“…አሁን ባለንበት ወቅት ተደጋግፈን የምናልፍበት እንጂ አንዱ በሌላዉ ላይ ጫና የሚፈጥርበት እንዳልሆነ ታውቆ የግል ትምህርት ቤቶች ከደንበኞቻቸዉ ጋር በመነጋገር እና በመግባባት እንዲሰሩ እያሳስብን በቀጣይም ይህን አልፈዉ በሚቀርበዉ ጥቆማ መሰረት ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የክፍያ ጭማሪ የሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች የሚኖሩ ከሆነ ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ቢሮው የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን” (ምንጭ የባለስልጣኑ ፌስቡክ ጽ)

ቂቂቂቂ…

ግን ይህ ባለስልጣን ምንድነው የሚያጨሰው በማምላክ ? እንዲህ ያለ ጡዘት በዘራችሁ አይድረስ!

መጀመሪያ “ወላጅና ትምህርት ቤቶች ይደራደሩ ጣልቃ አልገባም” አለ።  ዛሬ ደሞ “የተጋነነ ጭማሪ ያደረጉትን እቀጣለሁ”  አለ። በመካከል ጭማሪው ተደርጎ፣ ወላጅም እያለቀሰም ቢሆን ከፍሎ፣ ትምህርት ቤቱም ትምህርት ለመጀመር ተዘጋጅቶ ባለበት ሁኔታ ይህ መግለጫ “አላልክም ላለመባል ልበል” አይነት መሆኑ ነው?

ሜርድ!!

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top