Connect with us

ግብረኃይል ተቋቋመ!!

አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት

ህግና ስርዓት

ግብረኃይል ተቋቋመ!!

ግብረኃይል ተቋቋመ!!

በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ዙሪያ የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከል ፣ ህገ-ወጥነትን ለመግታት እና ገበያን ለማረጋጋት የሚያስችል የጋራ ግብረ-ኃይል ተቋቋመ::

በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ዙሪያ የፊንፊኔ ልዩ ዞን ከተሞች ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፍጠር በሸቀጦች ላይ ዋጋ እንዲጨምር በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ የሚያደርጉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ለመከላከል እና የህግ የበላይነትን ማስከበር በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል የጋራ ግብረ-ኃይል ተቋቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በጋራ ግብርኃይሉ ምስረታ ላይ እንዳስታወቁት ከጁንታው ጋር ትስስር የነበራቸው እና ጥቅማቸው የተነካባቸው አንዳንድ ነጋዴዎች በከተማዋ የተለያዩ የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመፈፀም የኑሮ ውድነት እና የገበያ አለመረጋጋት እንዲፈጠር እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በተለይ ምርት በህገ-ወጥ መንገድ በማከማቸት እና በመደበቅ፣ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው የምርቶች እና አገልግሎቶች የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ባደረጉ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ የንግድ ቢሮ ጋር የቁጥጥር ግብረ-ኃይል በማዋቀር ስራውን መምራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ሃላፊው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደንጌ ቦሩ በበኩላቸው ሀገራችን አሁን ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድነትና በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በተለይ በአጎራበች ከተሞችና አከባቢዎች ያሉ ፋብሪካዎች ምርታቸውን ወደ አዲስ አበባ በማጓጓዝ ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋር በሚዋሰንባቸው ክፍለ ከተሞች ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ ለሚ-ኩራ እና ጉለሌ ከተማ ክፍለ ከተሞች እና የልዩ ዞኑ ከተሞች እና አካባቢዎች የሚደብቁበት ሁኔታ እንዳለ አቶ ደንጌ ቦሩ ገልጸዋል፡፡

የጋራ ግብረኃይሉ በገጠፎ፤ሱሉልታ፤ሰበታ፤አላምገና፤ገላን እና ቡራዩ ላይ የሚያተኩር ሲሆን በዋናነት የማከማቻ መጋዘኖች ፍተሻ፣ ምርት አቅርቦት፣ ህግ ማስከበር እና ደረሰኝ ግብይት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ እና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አቶ ደንጌ ቦሩ ተናግረዋል፡፡

ግብረ-ኃይሉ አላስፈላጊ የምርት ክምችት እንዳይፈጠርና የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርት አቅርቦት ለማሻሻል አተኩሮ የሚሰራ ሲሆን በአዲስ አበባ በኩል ገቢዎች ቢሮ፣ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ፖሊስ ኮሚሽን፣ህብረት ስራ ኤጀንሲ፣የኦሮሚያ ከተሞችና አከባቢዎች አዋሳኝ ክፍለ ከተሞች፣ የህብረት ስራ፤የገቢ፤ የሰላምና ጸጥታ እና ፖሊስ ጽ/ቤቶች አንዲሁም በኦሮሚያ በኩል፣ ኦሮሚያ ንግድቢሮ፣ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ፣የኦሮሚያ ህብረት ስራ ኤጀንሲ የግብረ-ኃይሉ አባላት መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡(አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top