ሱዳን ህወሓትን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አሸማግላለሁ አለች
ሱዳን በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ሽምግልናን ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ሱዳን ትሪቢዩን ዘገበ።
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከወያኔ መሪዎች ጋር በመገናኘት ሁለቱ ወገኖች ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለማምጣት በሰላማዊ መፍትሄ ላይ ለመወያየት እና ለሲቪሎች ሰብዓዊ ዕርዳታ በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሽምግልና እንደሚጀምሩ በዘገባው ተጠቁሟል።
በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የጦርነት ቀጠናዎች ሀገሪቱን በሚያዋስኑበት እና ስደተኞች ወደ ሱዳን መግባታቸውን በመቀጠላቸው ሱዳን በኢትዮጵያ ውስጥ ለዘጠኝ ወራት እየተባባሰ የመጣውን ግጭት እያሳሰባት ነው።
የዩኤስኤአይዲ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ሰሞኑን ሱዳን በተገኙበት ወቅት የትግራይን ግጭት ለመፍታት የሱዳንን ተነሳሽነት እንደሚደግፉ መናገራቸው አይዘነጋም።
ፎቶ :-ፋይል /ጠ/ሚ አብደላ እና ጠ/ሚ ዐብይ
***
August 4, 2021 (KHARTOUM) – Sudan is preparing to launch a mediation between the Ethiopian government and the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), with the support of the international community.
Sudanese Prime Minister Abdallah Hamdok holds talks at the US Capitol in a landmark visit to Washington (AFP Photo JIM WATSON)The Sudan Tribune learned that Prime Minister Abdallah Hamdok is in contact with the Ethiopian government and the TPLF leaders to bring the two parties to the negotiating table to discuss a peaceful solution and allow humanitarian aid to civilians.
Hamdok, also, informed of his initiative the heads of the East African bloc IGAD, Eritrea and a number of friendly Western countries, including France and the United States of America.
Sudan is increasingly concerned about the nine-month-long escalating conflict in Ethiopia as the war zones in the Tigray and Amhara regions border the country and refugees continue pouring into Sudan.
Officials in Khartoum further say that this conflict might ignite other hotspots in the multiethnic country pointing to the western Benishangul-Gumuz region which is also bordering Sudan as was the case in December 2020.
USAID head Samantha Power, on Tuesday, said they support the Sudanese initiative to resolve the Tigray conflict….