Connect with us

የሱዳንን የውስጥ ፖለቲካ ከአገራችን ፖለቲካ ባልተናነሰ ደረጃ ልንከታተለው ይገባል

የሱዳንን የውስጥ ፖለቲካ ከአገራችን ፖለቲካ ባልተናነሰ ደረጃ ልንከታተለው ይገባል
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የሱዳንን የውስጥ ፖለቲካ ከአገራችን ፖለቲካ ባልተናነሰ ደረጃ ልንከታተለው ይገባል

የሱዳንን የውስጥ ፖለቲካ ከአገራችን ፖለቲካ ባልተናነሰ ደረጃ ልንከታተለው ይገባል

(በጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም)

ሱዳን፦

-ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ አንዷተዋናይ ናት።

-የኢትዮጵያን መሬት በጉልበት ወርራ ይዛለች።

-ህወሃትን እያሰለጠነች በመላክ ሰላም ተነሳለች።

-የጉሙዝና ሌሎችንም ጽንፈኛ ሃይሎች እያስታጠቀች ታሰማራለች።

-አሜሪካኖች ኢትዮጵያን ለማዳከም በጆከርነት ይስቧታል።

– ግብጽን ጨምሮ ሌሎች የአረብ አገራት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ሲፈልጉ የሚጠቀሙባት አገር ናት።

የሱዳን ህዝብ ደግ እና ኢትዮጵያን የሚወድ  ቢሆንም፣ መንግስቷ ግን አከርካሪ የለውም። ኑሮትም አያውቅም። ለእገሩ በቅኝ ግዛት የተገዙ አገሮች መንግስታት በአብዛኛው አከርካሪ የላቸውም።

 እንደ ግብጽ ወታደራዊ አዛዦች፣ የሱዳንም ወታደራዊ አዛዦች ነጋዴዎች ናቸው። ለገንዘብ ሲሉ የአገራቸው ደህንነት አሳልፈው ይሰጣሉ።

በሱዳን የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ጅምር ነው።  ትርምሱ ይቀጥላል። ወታደራዊ አዛዦቹ የሲቪሉን አስተዳደር አስወግደው ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ሳይቆጣጠሩ እንቅልፍ አይተኙም።

የሲቪሉ አስተዳደሩም ህልውና ለማቆየት ሲል፣ ህዝቡን አነሳስቶ፣ በወታደሩ ላይ ተቃውሞው እንዲደረግ ስራ መስራቱ አይቀርም። ወታደሩ የሲቪሉን አስተዳደር በሃይል አፍርሶ የህዝቡን ተቃውሞ ካዳፈነ በኋላ፣ እርስ በርሱ ይዋጋል።

በሱዳን የሚፈጠረውን ስርዓት አልበኝነት ተከትሎ በርካታ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ተጨማሪ ጫና ይፈጥራሉ። ቢሆንም ኢትዮጵያ የሱዳንን ጉዳይ በሩቁ እያየች በትዕግስት መጠበቅ እንጅ በየትኛውም መልኩ ጣልቃ መግባት አይኖርባትም። አጋጣሚውን አገኘሁ ብላ የተያዙባትን መሬት ለመመለስ ብትነሳ፣ ያልታሰበ ነገር ሊፈጠር ይችላል። 

የሱዳን ወታደራዊ አዛዦች “ኢትዮጵያ ወረረችን” ብለው፣ የሱዳንን ህዝብ ስሜት ሊያነሳሱበት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ከሲቪሉ የሚነሳባቸውን ተቃውሞውን ለማፈንና ስልጣናቸው ለማቆየት ሊረዳቸው ይችላል። ከዚህም አልፎ  የሱዳንን ብሄራዊ ስሜት ያነሳሳልናል ካሉ ተጨማሪ ትንኮሳ ሁሉ ሊፈጽሙ ይችላሉ።

የቱንም ያክል ቢዘገይ የተወሰደብን መሬት መመለሱ አይቀርም። ሱዳን በውስጥ ጉዳይዋ ስትተራመስ፣ በኢትዮጵያ ድንበር  ዙሪያ ያለውን ጦሯን ሰላም እንዲያስከበር ወደ ካርቱም መሳቧ አይቀርም። ያን ጊዜ የአርሶአደር ሚሊሺያዎችን ብቻ በመላክ መሬቱን፣ አንደኛ ያለ ደም መፋፈስ፣ ሁለተኛ ያለ ዲፕሎማቲክ ጫጫታና ሶስተኛ ወታደራዊ አዛዦች ለፖለቲካ ደጋፍ ሳይጠቀሙበት ማስመለስ ይቻላል።

የሱዳን የውስጥ ጉዳይ እየተበላሸ እንጅ እየተሻሻለ የሚሄድበት እድል ጠባብ ነው። ሱዳን  ብትረጋጋ እንኳን የህወሃትን ጦርነት ካጠናቀቁ በኋላ፣ ፊትን ወደ ካርቱም ማዞር ይቻላል። በየትኛውም መመዘኛ የሱዳን ሃይል የኢትዮጵያን ጦር መቋቋም የሚችልበት አቅም የለውም።

የኢትዮጵያ መንግስት በሽምግልና ወይም በሰላም አስከባሪ ስም ከእግዲህ ዲፕሎማቱን ወይም ጦሩን ወደ ሱዳን መላክ የለበትም።  የሱዳን መንግስት የሚታመን  አይደለምና።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top