Connect with us

ውድድሩ እስኪያልቅ እንኳ ለሀገር ውጤት ስትሉ ተግባብታችሁ ለመስራት ሞክሩ!!

ውድድሩ እስኪያልቅ እንኳ ለሀገር ውጤት ስትሉ ተግባብታችሁ ለመስራት ሞክሩ!!
Photo: Social media

ስፖርት

ውድድሩ እስኪያልቅ እንኳ ለሀገር ውጤት ስትሉ ተግባብታችሁ ለመስራት ሞክሩ!!

ውድድሩ እስኪያልቅ እንኳ ለሀገር ውጤት ስትሉ ተግባብታችሁ ለመስራት ሞክሩ!!

(ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋ)

የሁለቱ ፌዴሬሽኖች ተቀራርቦ አለመስራት የአትሌቶች ሞራል እየተጎዳ ለጉዞ የተዘጋጁ ሰዎች ከኤርፖርት እየተመለሱ ነው።

የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ ማንም ይሁን ማን ቀድሞ ማለቅ የሚገባው ጉዳይ ቁጭ ብሎ ተግባብቶና ስፖርቱን ማእከል አድርጎ (ኢትዮጵያን አስቀድሞ) መነጋገር አለመቻል በኤርፖርት አላስፈላጊ ድራማና የመግለጫ ልውውጥ አስከትሎአል።

በዚህ መሀል የባለውለተኛ ባለሙያዎችና የነገ ውጤታማ አትሌቶች ሞራል ብሎም የሀገር ክብር ይነካል። ለአንድ ሰአት ተነጋግሮ ሊፈታ የሚችል ጉዳይ የማይሽር ነገር ያስቀምጣል። ሀገር ውጤት ታጣለች፣ ገንዘብ ይባክናል።

የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቡድኑ ውስጥ መግባታቸው ተገቢ አይደለም ሲል መግለጫ ስለ ሰጠባቸው የሶስት ሺህ መሰናክል እና የአምስት ሺህ ሩዋጮች ወቅታዊ መረጃ ከቁጥሮች ጋር እያመሳከርን እንይ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለጫ

“አትሌት ለሜቻ ግርማ በዶኃ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባመጣው የተሻለ ውጤት ለ8 ወራት  የቡድኑ አባል ሲሆን በደረሰበት የእግር ጉዳት የመጀመሪያ ማጣሪያ አልተሳተፈም፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድርም አልተሳተፈም፣ የሄንግሎ ትሪያልም  መሳተፍ ያልቻለ በመሆኑ፡

በፌዴሬሽኑ ውሳኔ  ከተወዳዳሪነት የተሰረዘ” መሆኑን ቢገልፅም

ለሜቻ ግርማ ጀግና ሀይሌ ገብረስላሴ እንዴት ከቡድን ተቀነሰ ሲል የኢትዮ ስፖርት ጥያቄ ያነሳበት አትሌት ነው።

በርግጥም በፌዴሬሽን መግለጫ እንደተጠቀሰው  በህመም ምክንያት በ3000 ሜ መሰናክል በኢትዮጵያ ሻንፒዮናንና  እና በሄንግሎ ማጣሪያ  አልተሳተፈም።

ህመሙ ከግምት ውስጥ ገብቶለት በተጠባባቂ ተይዞ ነበረ። ነገር ግን በኦሎምፒክ የተመረጡ አትሌቶች ስም  ዝርዝር የመጨረሻ ነው ተብሎ  ከተላከ በኋላ  በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ በ3000ሜ መሰናክል  በመሮጥ በውድድሩም ፤በአመቱም፤ ለኦሎምፒክ ከተመረጡ  አትሌቶች ሁሉ የተሻለና ፈጣን  1ኛ ሰአት አስመዝግቦ ያሸነፈ አትሌት ነው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመግለጫው ስለ ሀጎስ ገ/ህይወት እንዲህ አለ:-

” በሄንግሎ ትሪያል የተወዳደሩና ውጤታማ የሆኑ አትሌቶችን በመለየት በወቅቱና በጊዜው ፌዴሬሽኑ ለኦሊምፒክ ኮሚቴው የላከ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ እውቅና ውጭ በ10ሺ ሜ በመወዳደር 4ኛ ደረጃ በማግኘት ተጠባባቂ የነበረው አትሌት ሃጎስ ገ/ህይወት ለፌዴሬሽኑ ሳያሳውቅ ከሆቴል ወጥቶ የሄደና በ5 ሺ ሜ Short List ውስጥ ተመዝግቦ  የታየ ሲሆን” ተቃውሞውን በመግለጫ አሳወቀ።

ታዲያ ሀጎስ ገ/ህይወት ፌዴሬሽኑ እንዳለው የኦሎምፒክ ማጣሪያው  በመረጠው ፊልድ  በሄንግሎ በ10,000 ሜ አራተኛ ሆኖ ጨርሷል። ነገር ግን  ከሄንግሎ ማጣሪያ በኋላ በሮም ዳይመንድ ሊግ በ5000ሜ ፈጣን ሰአት ያመጣ ሲሆን ይህም በፌዴሬሽኑ ለአምስት ሺህ ለኦሎምፒክ ከተመረጡ የ5000ሜ አትሌቶች ባለው ወቅታዊ ሰአት የተሻለ እና ፈጣን አንደኛ ሰአት ያስመዘገበ አትሌት ያደርገዋል።

ፌዴሬሽኑ በእኔ የአስር ሺህ የሄንግሎ ውድድር ስለወደቅህ በአምስት ሺህ ከሄንግሎ ውጪ በሮም ያመጣኸውን ሰአት አልቀበልም ነው ያለው ጥያቄው በልጁ ብቃት ሳይሆን የእኛን ደንብ አልተከተልክም ነው።

በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ መመረጡን የተቃወመው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ ነው።

“በ5 ሺ ሜ ማጣሪያ 5ኛ ደረጃን በመያዝ ከቡድኑ የተቀነሰ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በኦሊምፒክ ቡድኑ ውስጥ ተካቶ እንደሚጓዝ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረጉን አውቀናል” ይላል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የኦሎምፒክ ም/ፕሬዚዳንቱ ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ ከኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ መግባት አለበት ሲል የተከራከረለት ሌላው አትሌት ደግሞ ሙክታር እድሪስ ነው።

ሙክታር እድረስ  የሄንግሎውን ማጣሪያ በ5000ሜ 5ኛ ሆኖ ጨርሷል።

ከሄንግሎ ማጣሪያ ወዲህ በተደረጉ ውድድሮች ወደ ቀድሞ አቋሙ የተመለሰ  አጨራረስ የሚችል ፈጣን አትሌት ነው። ሲል ሀይሌ ገብረ ስላሴ ያደንቀዋል።

በተቀነሱትና የሚጨመሩት አትሌቶች መካከል ፀብ ሳይፈጠር እንደ ሌባና ፖሊስ መደባበቅ ሳያስፈልግ ማለቅ የሚችልን ውሳኔ በእህልህ እዛና እዚህ ሆነው በመግለጫ እያወሩ ነው።

ውድድሩ እስኪያልቅ እንኳ ለሀገር ውጤት ስትሉ ተግባብታችሁ ለመስራት ሞክሩ።

 

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top