Connect with us

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያደረገው ምርጫ ሕገ ወጥ ነው አለ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያደረገው ምርጫ ሕገ ወጥ ነው አለ
አብመድ

ስፖርት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያደረገው ምርጫ ሕገ ወጥ ነው አለ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያደረገው ምርጫ ሕገ ወጥ ነው አለ

 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ትናንት ባደረገው የምርጫ ጉባኤ የሥራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል። አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶክተር)ን በድጋሜ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ መርጧል።

ከወራቶች በፊት ሃዋሳ ላይ በነበረው ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ከኦሎምፒክ ማግስት እንዲደረግ መወሰኑ ይታወቃል።

ነገር ግን ኦሎምፒክ ኮሚቴው ድጋሜ ቢሾፍቱ ላይ ባደረገው ጉባኤ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ከቶኪዮ ኦሎምፒክ በፊት እንዲካሄድ ወስኖ በ20/07/2013 ዓ.ም ምርጫ አካሂዷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ለቶኪዮ ኦሎምፒክ የተመረጡ አትሌቶችም ምርጫውን በይፋ ተቃውመዋል። በጉዳዩ ላይ ዛሬ ፌዴሬሽኑ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ፕሬዝዳንቷ አትሌት ደራርቱ ቱሉ የተደረገው ምርጫ ህገወጥና የቶኪዮ ዝግጅት መንፈስን የሚረብሽ ነው ብላለች።

ምርጫውን በተመለከተ ኦሎምፒክ ኮሚቴው ያወጣቸው አዳዲስ ሕግና ደንቦች  የዓለም አቀፉን ኦለምፒክ ኮሚቴ መመሪያ የጣሱ ናቸው ተብሏል።

መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ ችግሩ እስኪፈታ ድርስ ተቃውሞ እንደሚያሰሙ የኢትዮያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቷ ደራርቱ ቱሉ ተናግራለች።

ፌደሬሽኑ ምርጫውን በመቃወም ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫም አውጥቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቶች ማኀበር ፕሬዝዳንት አትሌት ማርቆስ ገነቴ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሕገ ወጥ አሠራር ሀገሪቱን ከኦሎምፒክ እንዳያሳግዳት ስጋት እንዳለው ጠቁሟል።(አብመድ)

 

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top