Connect with us

የኦሎምፒክ ውጤት ለምን ራቀን?

Social media

ስፖርት

የኦሎምፒክ ውጤት ለምን ራቀን?

የኦሎምፒክ ውጤት ለምን ራቀን?

ትላንት ለሊቱን በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወንዶች ማራቶን ውድድር የተሰለፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድራቸውን ማጠናቀቅ ሳይችሉ ቀርተዋል።
ሹራ ቂጣታ ከ9 ኪ.ሜ. በኋላ፣ ሲሳይ ለማ ከ23 ኪ.ሜ. በኋላ፣ ሌሊሳ ደሲሳ ከ30 ኪ.ሜ. በኋላ መቀጠል አልቻሉም።

ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ በ2:08.38 አንደኛ በመውጣት የኦሊምፒክ ሻምፒዮንነት ክብሩን ባስጠበቀበት ውድድር ኔዘርላንዳዊው አብዲ ናጌዬ (2:09.58) ሁለተኛ፣ ቤልጂየማዊው ባሺር አብዲ (2:10.00) ሶስተኛ ወጥተዋል።

የወንዶች ማራቶን ውድድሩን ከጀመሩት 106 አትሌቶች 76ቱ ሲጨርሱ 30 አትሌቶች አቋርጠዋል፡፡

ለሊቱን በተጠናቀቀው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና በሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡

**ስለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ምን ተዘግቦ ነበር?

ቶኪዮ ከተጓዘው ከ100 በላይ የኦሎምፒክ ልዑካኑ ግማሹ ያህሉ ጥያቄ እያስነሳ ይገኛል!- አትሌቶች ተቀንሰው ለምን ልዑካኑ በዛ?

  1. የ32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮሮና ምክንያት በተደጋጋሚ ሲራዘም ቆይቶ በቅርቡ በታዋቂው የጃፓን አርክቴክት ኬንጎ ኩማ በተሠራው ባለ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በፈጀው እና 68ሺ ተመልካች በሚይዘው ስታዲየም ያለ ተመልካች በሚደረግ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በይፋ ሲካሄድ መክረሙ ይታወሳል።

የቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ልዑካን አጠቃላይ ከ100 በላይ እንደተጓዘ ተዘግቧል ። ይህም በአትሌቲክስ ፌደረሽን በኩል 35 አትሌቾች 11 አሰልጣኞች ፣ 2 ሐኪሞች ፣ 3 ወጌሻዎች እና 4 ኦፊሻሎች በአጠቃላይ 55 የልዑካን ቡድን መጓዛቸው ተጠቁሟል። ከዚሁ በድን በቀጣዮቹ ቀናት የሚጓዙ አትሌቶች እንዳሉ ታውቋል።

በሌሎች ስፖርቶች በውሀ ዋና ከአሰልጣኝ እና ከቡድን መሪ 3 ፣ ተኳንዶ በተመሳሳይ 3 ፣ ብሰክሌት እንዲሁ 3 ስፖርተኞች ብቻ ወደ ቶኪዮ መጓዛቸው ተገልጿል።

በተቃራኒው በኢትዮጵያ ልዑካን በኩል አጠቃላይ ከተጓዘው ከ100 በላይ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ብዙም ከስፖርት ጋር ግንኙነት የሌላቸው በልዑካን ቡድንነት መጓዛቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።

እንደ መረጃውን ከሆነ በኮቪድ ምክንያት አትሌቶች ቢታመሙ በምትካቸው ተጠባባቂ አትሌቶች በመቀነሳቸው እና ያለመጓዛቸው ተጠቁሟል።

ከላይ የተጠቀሱት ተጠባባቂ አትሌቶች ተቀንሰው ለምን የልዑካን ቡድኑ እንደበዛ ከውድድሩ በኋላ ማብራሪያ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው።

ይህን እና ተያያዥ በርካታ ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን አምቆ ወደ ጃፓን የተጓዘው ልዑካን ቡድን የተጠበቀውን ያህል ውጤት ሳያገኝ መቅረቱ በአሁን ሰዓት መነጋገርያ ሆኗል። ውጤት ሊርቀን የቻለው ከስፖርት ዘርፍ አመራሩ ድክመት ጋር ተያይዞ ይኾን? ይኸንንም መጠየቅና በቅጡ መፈተሽ ይገባል።

(መነሻ ምንጭ:- ስፖርት ኢትዮጵያ፣ ኢትዮ ኪክኦፍ)

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top