Connect with us

ብልፅግና በምርጫው የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫው የተፎካከሩ ፓርቲዎችን በመንግስት መዋቅር ስር ያሳትፋል-ጠ/ሚ አብይ አህመድ

ብልፅግና በምርጫው የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫው የተፎካከሩ ፓርቲዎችን በመንግስት መዋቅር ስር ያሳትፋል-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
ኢዜአ

ዜና

ብልፅግና በምርጫው የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫው የተፎካከሩ ፓርቲዎችን በመንግስት መዋቅር ስር ያሳትፋል-ጠ/ሚ አብይ አህመድ

ብልፅግና በምርጫው የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫው የተፎካከሩ ፓርቲዎችን በመንግስት መዋቅር ስር ያሳትፋል-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
ብልፅግና ፓርቲ በምርጫው የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫው የተፎካከሩ ፓርቲዎችን በየደረጃው ባለው የመንግስት መዋቅር የሚያሳትፍ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
የሲቪክ ማህበራት ደርጅቶች ምክር ቤት በዘንድሮው ምርጫ ለተፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አብይ አህመድ በምርጫ ፉክክሩ ፓርቲያቸው አሸናፊ ከሆነ ተፎካካሪ የነበሩ ፓርቲዎችን ከታች ጀምሮ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሳትፋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ዘንደሮ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ የቻለችው ሁላችንም ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ በመስራታችን ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በምርጫው እለት ዜጎች ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን ወጥተው ድምፅ በመስጠታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያዊያን ከፖለቲካ ይልቅ አገር ትቀድማለች የሚል መርህ አንግበው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ አገራቸውን አሸናፊ አድርገዋልም ነው ያሉት።
የሲቪክ ማህበራት ደርጅቶች ምክር ቤት በምርጫው ለተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባዘጋጀው የምስጋና ምሽት የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።(ኢዜአ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top