Connect with us

መንግስት ወቃሽ ኾኖ መምጣቱ  ትክክል አይደለም

ወገን እንቁረጥ?!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

መንግስት ወቃሽ ኾኖ መምጣቱ  ትክክል አይደለም

መንግስት ወቃሽ ኾኖ መምጣቱ  ትክክል አይደለም

(ፋሲል የኔዓለም)

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋዜጠኞችንና አክቲቪስቶችን መውቀሳቸው ትክክል አይመስለኝም። አንድ ሰራዊት ከመቀሌ በድንገት ለቆ ሲወጣ ሊፈጠር የሚችለው ስሜት ቀላል አይሆንም። የኢትዮጵያ ህዝብ በጦርነቱ ከባድ መስዋትነት ከፍሏል።  

የተበተነው ሃይል እንደገና ተሰባስቦ መቀሌን ተቆጣጠረ ሲባል የሚፈጥረው ግርምት ብቻ ሳይሆን ድንጋጤም ቀላል አይደለም።

መንግስት የራሱን ስራ መስራት ሲሳነው ወቃሽ ሆኖ መምጣቱ ትክክል አይደለም። እንዲህ አይነት ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል ለህዝቡ አስቀድሞ በተለያዩ መንገዶች ፍንጭ መስጠት በተገባ ነበር። ይህ ግን አልሆነም። 

ታዲያ ተወቃሽ መሆን ያነበረበት ማን ነው? ተወቃሽ ወቃሽ ሆኖ መምጣቱ፣ ከድክመት ያለመማርና ዜጎች በቂ መረጃ ሳይኖራቸው እንደፈለጉ አስተያየት እንዲሰጡ እንዲሁም መንግስት እስኪናገር ብቻ እንዲጠብቁ የሚያደርግ የተሳሳተ አካሄድ ነው።

ምናልባት አንዳንዶች  መንግስት እንዲህ አይነት እርምጃ ሊወስድ ማሰቡን በተለያዩ መንገዶች ሰምተው ይሆናል።  መረጃውን በፍጥነት ቢሰጡ  ኖሮ ህዝቡ ግራ ላይጋባ ይችል ነበር። ግን ደግሞ እንዲህ አይነት ወሳኝ መረጃዎችን አስቀድሞ ማውጣቱ፣ በአገሪቱም ሆነ በሰራዊቱ ላይ ያልተጠበቀ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል በሚል መንግስት እራሱ እስኪናገረው አፍነውትም ይሆናል። 

እንዲህ ያደረጉ ጋዜጠኞች እንዳሉም አውቃለሁ።

መንግስት አስቀድሞ ፍንጭ መስጠቱ ጉዳት ያመጣል ብሎ ቢያስብ እንኳን፣  እርምጃውን ከወሰደ በኋላ ወዲያውኑ መረጃ መስጠት ነበረበት። ከመወቃቀስ ይልቅ ለመማማር መፍጠን ይገባል። መንግስት የራሱን ድክመት አውቆ ለማረም መዘጋጀት እንጅ፣ ሌሎችን በመውቀስ ድክመቱን ለመሸፈን የሚሞክር ከሆነ፣ ለአሉባልታና መሰረት ለሌላቸው ትንተናዎች ጥቃት  ተጋላጭ መሆኑ ይቀጥላል።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top