Connect with us

ምርጫው ሰላማዊ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ መንግስት ድርብ ሃላፊነት አለበት– ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ምርጫው ሰላማዊ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ መንግስት ድርብ ሃላፊነት አለበት-- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
Ethiopian News Agency

ዜና

ምርጫው ሰላማዊ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ መንግስት ድርብ ሃላፊነት አለበት– ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ምርጫው ሰላማዊ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ መንግስት ድርብ ሃላፊነት አለበት– ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ መንግስት ድርብ ሃላፊነት አለበት፤ ይህንንም ለመወጣት ዝግጁ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የመራጮች ምዝገባ እንደሚራዘም ጠቁሟል።

በምርጫው ሂደት አስካሁን የነበሩትን ክንውኖች በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርእሳነ መስተዳድሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ በውይይቱ ላይ አንዳነሱት የኢትዮጵያ ጠላቶች ምርጫውን ለማስተጓጎል፣ ደካማና የሚያዙት መንግስት ለመፍጠር ሌት ተቀን እየሰሩ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል።

የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ አንዲካሄድ መንግስት ድርብ ሃላፊነት አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በውይይቱ ላይ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች በምርጫው ሂደት የእስካሁኑን ክንውን ሪፖርት አቅርበዋል።

በእስካሁኑ ሂደት የመራጮች ምዝገባ ተሳትፎ በጥሩ ሁኔታ የተከናወነባቸው ክልሎች መኖራቸው ተመልክቷል።

በሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች የመራጮች ምዝገባ ከ80 በመቶ በላይ አፈፃፀም መኖሩን አብራርተዋል።

በሌሎች ክልሎችም የመራጮች ምዝገባ አፈፃፀም ከ50 በመቶ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የመራጮች ምዝገባ እንደሚራዘም ጠቁመዋል።

ተጨማሪው ቀን ምን ያክል እንደሚሆን ግን ቦርዱ ተወያይቶ የሚወስን እና የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጸዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top