Connect with us

#ኢዜማ ስለአጣዬ የንፁሀን ጥቃት

ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው!
የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት

ዜና

#ኢዜማ ስለአጣዬ የንፁሀን ጥቃት

#ኢዜማ ስለአጣዬ የንፁሀን ጥቃት

“የችግሩን ምንጭ በአግባቡ መለየት እና ማረቅ ካልተቻለ መፍትሄ መስጠት አይቻልም!”

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በየአቅጣጫው በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና የንብረት መውደም መፍታት ያልተቻለው የችግሩን ምንጭ በአግባቡ ካለመለየት እና ከመሰረቱ ከመፍታት ይልቅ መንግሥት ሁል ግዜ ዜጎች ላይ አደጋ ከደረሰ በኋለ እሳት ማጥፋት ላይ ትኩረት በማድረጉ ነው።

በአጣዬ እና በዙርያዋ ባሉ ከተሞች ከትላንት በስትያ ጀምሮ በዜጎች ላይ በታጣቂዊች በተከፈተ ጥቃት ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል፣ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ይሄ ዓይነቱ ጥቃት በዚህ አካባቢ ሲደጋገም መንግሥት የችግሩን ምንጭ መርምሮ ከምንጩ ከማድረቅ ይልቅ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ሠራዊት ሲያዘምት እና የተረጋገ ሲመስለው ሠራዊት ሲያሰወጣ ተመልክተናል። ይሄ የተረጋጋ አካባቢያዊ ሁኔታ ለመፍጠር እና የዜጎችን በሰላም የመኖር መብት ለማስከበር ትክክለኛ አካሄድ አይደለም።

ኢዜማ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ እንደነበረው የመንግሥት መጀመሪያ ተግባር የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ማስከበር ነው፤ ሆኖም በሀገራችን በተመረጡ ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ዓይነት ጥቃት በዜጎች ላይ እየደረሰ ነው። ይህ፣ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት የሄደበት መንገድ ልክ እንዳልሆነ አመላከች ሲሆነ በተለይ ከነዚህ ግጭቶች ጀርባ በሶስተኛ ወገን ላይ ጣት ከመቀሰር ይልቅ የመንግሥተን አስተዳደራዊ እና የፀጥታ ዘርፎች በአግባቡ መመርመር ተገቢ ነው ብለን እናምናለን።

ኢዜማ መንግሥትን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት በአካባቢው ሕግ ለማስከበር እና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪውን ያቀርባለን።

በጥቃቱ ሕይወታቸውን ባጡት ዜጎች የተሰማን ሀዘን ጥልቅ ነው። ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ለመላው  ሀገራችን ሕዝብ መፅናናትን እንመኛለን።

የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top