Connect with us

ከ29 ሺ በላይ የአዲስአበባ ነዋሪዎች ወደዘላቂ ኑሮ ተሸጋገሩ

ከ29 ሺ በላይ የአዲስአበባ ነዋሪዎች ወደዘላቂ ኑሮ ተሸጋገሩ
አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት

ዜና

ከ29 ሺ በላይ የአዲስአበባ ነዋሪዎች ወደዘላቂ ኑሮ ተሸጋገሩ

ከ29 ሺ በላይ የአዲስአበባ ነዋሪዎች ወደዘላቂ ኑሮ ተሸጋገሩ

29 ሺ 410 ነዋሪዎች በመጀመሪያ ዙር የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተጠቃሚ በመሆን  ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ መርሐግብር ተሸጋገሩ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በ2009 ዓ.ም በከተማዋ ተግባራዊ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር የምግብ ዋስትና ፕሮግራም 29 ሺ 410 ተጠቃሚዎች ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ መሸጋገር ችለዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የተቋማት አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በሶስት ዓመት ውስጥ ከ400 ሺህ ተጠቃሚዎች መካከል 16 በመቶ የሚሆኑት የቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ከተሸጋገሩት ውስጥ  ለ23 ሺ 616   በገንዘብ አያያዝ፣ በህይወት ክህሎት፣ በንግድ ስራ፣ በቴክኒክና ሙያ  ዘርፎች  ስልጠናዎች የተሰጣቸው ሲሆን በዚህም  በንግድ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአገልግሎት፣ በከተማ ግብርና እና በቅጥር ዘርፍ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡

በዚህ መርሀግብር የሚሳተፉ ዜጎችንም በዘላቂነት ኑረአቸውን እንዲመሩ  የከተማ አስተዳደሩ አስፋላፊውን ክትትል እና ድጋፍ ያደረጋል፡፡

በቀጣይም በተለያዩ ዙሮች በምግብ ዋስትና ፕሮግራም  የታቀፉ ከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ነዋሪዎችን  ተጠቃሚ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በምግብ ዋስትና ፕሮግራም በሶስቱ ዙር በ121 ወረዳዎች 415 ሺ 923 ተጠቃሚዎች ማስጠቀም የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ በማህበረሰብ አቀፍ ልማት ስራዎች 349 ሺ 375 እና በቀጥታ ድጋፍ ደግሞ  66 ሺ 548 ከድህነት ወለል በታች የነበሩ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡(የአ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top