Connect with us

ዜጎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት  በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲጣራ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

ዜጎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲጣራ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ
አሚኮ

ዜና

ዜጎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት  በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲጣራ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

ዜጎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት  በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲጣራ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣ እናት ፓርቲ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በጋራ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተፈጸመ ያለውን ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በዜጎች ላይ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ጥቃት እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በጋራ የአቋም መግለጫቸውም በሀገሪቱ ውስጥ በበርካታ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና በአጠቃላይ “መጤ” ተብለው በተፈረጁ ዜጎች ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተፈፀመ ያለውን ዘር ተኮር ጥቃት በጥብቅ እንደሚያወግዙ ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥትና የክልሎቹ መንግሥታት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው፣ የችግሩን ግዝፈትና መደጋገም እንዲሁም በሀገሪቱ አንድነትና ደኅንነት ላይ የደቀነውን ከፍተኛ አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ዘላቂ እልባት የመስጠቱ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለልተኛ ኮሚሽን በማቋቋም በጥልቀት መርምሮ ውጤቱንም ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ “በሀገር አንድነት እና ደኅንነት ላይ የተጋረጠው አደጋ” አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያሻው በማመን የመፍትሄ አካል ለመሆን እና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመንግሥት በኩል እስካሁን በተፈፀሙት ጥቃቶች ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ እንዲሁም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግሥት አመራሮች ሆነው የመከላከል ኃላፊነታቸውን ያልተወጡና በጥቃት የተሳተፉትን በሚመለከት በፍጥነት ተገቢው የማጣራት ሥራ እንዲሠራና በሕግ እንዲጠየቁ እንዲደረግም ጠይቀዋል፡፡

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ አሰላለፎች ውስጥ ተካትተው ዘርና እምነት ተኮር ጥቃቶችን የሚፈፅሙ አካላትን ለማውገዝ፣ ለማጋለጥ፣ እና ለመከላከል ብሎም ለማሸነፍና በሕግ ጥላ ስር ለማዋል በአንድነት እንዲቆሙ፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በአማራ ሕዝብ ላይ በጥላቻ ኃይሎች እየተፈፀመ ያለውን ዘር ተኮር ጥቃት ለማውገዝ፣ ለማጋለጥና ለፍርድ ለማቅረብ ያለምንም ልዩነት በጋራ እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተፈፀሙት ጥቃቶች ምክንያት ደጋፊ ወገኖቻቸውን ላጡና በጅምላ ተፈናቅለው ችግር ላይ ለወደቁት ወገኖች በአስቸኳይ የነፍስ አድንና የመልሶ ማቋቋም የተቀናጀ ርብርብ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢና በቤኒሻንጉል ክልል በተፈፀሙት ዘር ተኮር ጥቃቶች ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ  የተለያዩ ጉዳቶች ለደረሰባቸው ማገገምን እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡(አሚኮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top