Connect with us

የጠ/ሚ ዐብይ የድጋፍ ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

የጠ/ሚ ዐብይ የድጋፍ ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ
Ethiopian press agency

ዜና

የጠ/ሚ ዐብይ የድጋፍ ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

የጠ/ሚ ዐብይ የድጋፍ ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

ነገ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሁን ወዳሉበት ሃላፊነት የመጡበትን ሶስተኛ ዓመት አስመልክቶ በተሸከርካሪ ሊካሄድ የታቀደው የድጋፍ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አስተባባሪ ኮሚቴው ገለጸ፡፡

ከአስተባባሪ ኮሚቴው መካከል አቶ ሞቲ ሞሮዳ እንደገለጹት፤ ዛሬ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በተደረገው ምክክር የኮቪድ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን ተገልጿል፡፡

በተሸከርካሪ የድጋፍ ሰልፍ በሚካሄድበት ወቅትና የተሸከርካሪ ድምጽ በሚሰማበት ጊዜ ህብረተሰቡ ወደ መንገድ መውጣቱና መሰብሰቡ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ ለስርጭቱ መስፋፋት የበኩሉን ድርሻ ሊያበረክት ይችላል በሚል ጤና ሚኒስቴሩ ስጋቱን መግለጹን አቶ ሞቲ አመልክተዋል፡፡

“በመሆኑም ሃሳቡን በመቀበል የድጋፍ ሰልፉን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተወስኗል” ብለዋል፡፡

አዲሱ ለውጥ በኢትዮጵያ የተገኘው ከሶስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ለውጡን በማስመልከት በህዝቡ ተነሳሽነት የተዘጋጀ መርሃ ግብር ነበር ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

እዚህ እዛም እየተሰማ ያለው ችግር ከየትም መጥቶ ሳይሆን በራሳችን ነው ያሉት አቶ ሞቲ፤ ከምንጎዳዳ ይልቅ ብንተጋገዝና አንድ ብንሆን የተሻለ ነው የሚልና ለተገኘው ሰላምና አንድነት ምስጋና ለማቅረብና መልዕክት ለማስተላለፍ የታቀደ መርሃ ግብር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የአለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ለሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ ህዝቡ ከጎናቸው ቆሞ ድጋፍ እንዲያደርግና ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የታሰበ መርሃ ግብርም እንደነበርም አስታውቀዋል፡፡(ኢፕድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top