Connect with us

#ለገንቢዎች

#ለገንቢዎች
አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት

ዜና

#ለገንቢዎች

#ለገንቢዎች

በአዲስአበባ ከተማ ግንባታ በማከናወን ላይ ለሚገኙ ገንቢዎች 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በፕሮግራም  እንደሚሰራጭ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ::

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከንግድ ሚነስቴር  በሰጠው አቅጣጫ መሰረት በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ በከተማዋ ከ377 ብር በታች ዋጋ  ሲሚንቶ እንዲከፋፈል መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ግንባታ በማከናወን ላይ ለሚገኙ ገንቢዎች የሲሚንቶ ፍላጎትን በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ  እንዲያስችል በሁሉም ክፍለ ከተሞች በፕሮግራም ስርጭት እንደሚደረግ  የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሚኤሳ ገልጸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት 

  • ዛሬ ማክሰኞ በ21/7/13 ዓ.ም የካና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
  • ዕሮብ በ22/7/13 ዓ.ም አዲስ ከተማና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
  • ሀሙስ በ23/7/13 ዓ.ም ቦሌና አራዳ ክፍለ ከተማ
  • አርብ በ24/7/13 ዓ.ም ኮልፌና ልደታ ክፍለ ከተማ
  • ቅዳሜ በ25/7/13 ዓ.ም ለሚኩራና ጉለሌ ክፍለ ከተማ 
  • እሁድ በ27/7/13 ዓ.ም ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የግል ገንቢዎች  መስተናገድ እንደሚችሉ ተገልፆል፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም የግል ገንቢ በኢትዮጲያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በቅሎ ቤት ዋናው መስሪያ ቤት ህጋዊ ካርታና የግንባታ ፍቃድ ማሳየት እስከ ሰላሳ ኩንታል ሲሚንቶ መግዛት እንደሚችሉ አቶ ዳንኤል ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች አማካኝነት የቀረበ 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ ከ377 ብር በታች ዋጋ የተተመነለት ሲሆን ደርባ 343.35 ሳቲንም  ሙገር 352.63 ሳንቲም እና ሐበሻ 364.39 ሳንቲም  እንዲሸጥ መወሰኑን ህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ተናግረዋል፡፡(አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top