Connect with us

ዳመናን ማዝነብ (cloud seeding)

ዳመናን ማዝነብ (cloud seeding)
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

ዜና

ዳመናን ማዝነብ (cloud seeding)

ዳመናን ማዝነብ (cloud seeding)

ሀገራት የዝናብ/ውሃ እጥረታቸውን ለመፍታት ከከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ እስከ ደመና ማዝነብ የደረሱ የተለያዩ አማራጮችን ይጠቀማሉ።

ደመና ማዝነብ እየተለመደ የመጣ የሳይንስ ግኝት ነው። ደመና ከመሬት ከፍ ብሎ በሚገኝ ከባቢ ላይ በትነት መልክ የሚገኝ የውሃ ስብስብ ቅንጣት ነው። ይህ በሚሊዮን የሚቆጠር ወደዝናብ ያልተቀየረ ነጠብጣብ/ቅንጣት በንጥረ ነገር ርጭት አማካኝነት ከነጠብጣቡ ከፍ ብሎ እንዲያድግና ወደ መሬት ዝናብ ሆኖ እንዲወርድ ማድረግ ይቻላል። ይህ ነው ዳመና ማዝነብ (cloud seeding) የሚባለው። 

ደመና ያለበት አካባቢ ላይ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ይደረጋል። ንጥረ ነገሩ (ሲልቨር አይወዳይድና ፖታሺየም አይወዳይድ) ተበታትኖ የነበረው ደመና ላይ ሲያርፍ ደመናው እንዲሰበሰብና ወፈር ወዳለ የውሃ እንክብል እንዲቀየር ያደርገዋል። ይህ የውሃ እንክብል በመሬት ስበት አማካኝነት ወደ መሬት እንዲዘነብ ይገደዳል።

የንጥረ ነገር ርጭቱ ሀገራት እንዳላቸው አቅም ከመሬት ወደ ደመናው መርጭትም የሚቻልባቸው ሁኔታዎች አሉ። በሮኬት መልክ መተኮስ የሚቻል ሲሆን በሰው አልባ አውሮፕላኖችም ርጭት ማድረግ ይቻላል። የተለመደው ግን በአውሮፕላን ከደመናው በላይ አልያም በታች እየበረሩ መርጭት ነው።

ኢትዮጵያ ሰሞኑን የሞከረችው በአውሮፕላን የሚረጨውን ሲሆን ከደመናው ስር በመሆን ንጥረ ነገሩን በአውሮፕላን የሚረጭበት ነው። የተለያዩ የዳመና አይነቶች ሲኖሩ ይህኛው ዳመና የሚስብ/የሚነፍስ ንፋስ ስላለው ንጥረ ነገሩ ከስሩ ሲረጭ ከደመናው ጋር ወስዶ ይቀላቅለዋል።

ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ከመሬት ላይ በሚተከል “ግራውንድ ጀነሬተር” አማካኝነት ዝናብ ማዝነብ ሲሆን እዚህ ላይም ኢትዮጵያ ስራዎችን እየሰራች ነው። ንጥረ ነገሩን የሚረጭ “ግራውንድ ጄነሬተር” እንጦጦ ላይ ተከላ እያካሄደች ነው። ይህኛው አሰራር ተራራማ ቦታዎች ላይ ተተክሎ ከመሬት ቅርብ ወደ ሆነ ዳመና ንጥረ ነገር እንዲረጭ የሚደረግበት ነው። ቁጥጥሩ ደግሞ ከሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ባለ ማዕከል ላይ ይደረጋል።

ይህንን ስራ ለመስራት ኢትዮጵያ የተጠቀመችው ንጥረ ነገር በዋጋው ዝቅተኛ የሆነውን ሶዲየም ክሎራይድና ፖታሺየም ክሎራይድ ድብልቅ  (ሃይድሮስኮፒክስ) የተሰኘውን ንጥረ ነገር ነው።

ይሄ ቴክኖሎጂ በተፈጥሮ የሚገኝ ደመናም ይፈልጋል። አየር ላይ ደመና ከሌለ ዝናብ ማመንጨት አይቻልም። ቴክኖሎጂው ደመና መፍጠር የሚያስችል አቅም ላይ አልደረሰም።

ይህንን ከደመና ዝናብ የማመንጨት ቴክኖሎጂ እስራኤል፣ ቻይናና ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ በተለያየ መልኩ ይጠቀሙበታል። በርሃማ ቦታዎቻቸውን ማልማትም ችለዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ስታውል ዩናይትድ አረብ ኢምሬት የተለያዩ ድጋፎን አድርጋላታልች። የኢትዮጵያ ባለሙያዎችም በሰፊው ተሳትፈውበታል። ከበረራ ጋር በተያያዘም የኤፌድሪ አየር ሃይል የጥገና ባለሙያዎችና አብራሪዎች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያስጀመሩትና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራው ይህ ስራ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ፣ የተፋሰስ ባለስልጣን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎ ማዕከል፣ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት፣ የኢንፎርሜን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ከግሉ ዘርፍ ድሮን ላይ የሚሰሩ ቡድኖች ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ዓለም ላይ ያለውን ቴክኖሎጂ መጠቀም ብቻ ሳይሆን መፍጠርንም መማር አለባት የሚሉት የኤኖቬሽናን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያም ይህንን ቴክኖሎጂ በረሃማ ቦታዎችን ለማልማት በሰፊው ጥቅም ላይ ታውለዋለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በረሃማና ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያለባቸው አካባቢዎችን ለማልማት የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ሂደት በቅርቡ እንደሚጀመር ይፋ አድርጋ ነበር።(ምንጭ፡- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top