Connect with us

በአዲስ አበባ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ

በአዲስ አበባ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ

ዜና

በአዲስ አበባ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ

በአዲስ አበባ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ

በአዲስ አበባ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን ለማስቅረትና በመዲናዋ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስችላል የተባለ መመሪያ ተዘጋጀ።

መመሪያውን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ እና የከተማዋ የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ኮሚሽን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በ6 ክፍለ ከተሞች፣ በ4 ወረዳዎች እና በ306 ብሎኮች አርሶ አደሮች እየኖሩ መሆኑ በመግለጫው ተመልክቷል።

አርሶ አደሮቹ በቀደሙት ዘመናት ከተማዋ እየሰፋች በሔደች ቁጥር እየተገፉና ተገቢ ካሳ ሳያገኙ መተዳደሪያ የሆነውን መሬታቸውን ይለቁ ነበርም ነው የተባለው።

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚልኬሳ ጃጋማ እንደሚሉት አሁን የተዘጋጀው መመሪያ ቁጥር 20 /2013 ዓ.ም እነዚህን ችግሮች ይፈታል።

የመመሪያው መዘጋጀት ህግ-ወጥ የመሬት ወረራን ለማስቀረትና የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሆኑንም አብራርተዋል።

በራሳቸው ይዞታ ላይ የግብርና ስራ እያከናወኑ ያሉ አርሶ አደሮች ‘የግብርና መጠቀሚያ ሰርተፊኬት’ ይሰጣቸዋል በመመሪያው መሰረት።

አንድ አርሶ አደር ከአጠቃላይ ይዞታው ላይ በ500 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማከናወን እንዲችል በመመሪያው ተቀምጧል።

ከዚህ ጎን ለጎን የአርሶ አደር ልጆች በ150 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የመኖሪያ ቤት መገንባት እንዲችሉም እድል ይፈጥርላቸዋል ተብሏል።

ይህ መሆኑ አርሶ አደሩ የባለቤትነት መብቱ ተረጋግጦ በሕጋዊ ይዞታው ላይ በሚመቻውና በቻለው መልኩ መልማት ያስችላል ብለዋል አቶ ሚልኬሳ ።

የአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ በበኩላቸው የግብርና መጠቀሚያ ሰርተፍኬት አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎ ለትክክለኛው ሰው ይሰጣል ብለዋል።

ይህም አርሶ አደሩ ይወክለኛል ብሎ በየደረጃው በመረጠው ኮሚቴና በሌሎችም መንገዶች ማጣራት እንደሚደረግ በመመሪያው መካተቱን ነው የተገለጸው።

ሂደቱ በከተማዋ የሚደረገው ልማት ሰው ተኮር እንዲሆንና ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ከልማቱ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችላልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

(አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top