Connect with us

የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት ሶስት የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች ተመረጡ

የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት ሶስት የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች ተመረጡ
Photo: Social media

ዜና

የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት ሶስት የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች ተመረጡ

የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት ሶስት የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች ተመረጡ

~ ኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን የለበትም፣

የምርጫ ክርክርን እንዲያዘጋጁ ከተመረጡ 11 ድርጅቶች መካከል ሶስት ያህሉ የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  አስታወቀ።

ቦርዱ ባወጣው የፍላጎት ማቅረቢያ ቀነ ገደብ 23 ድርጅቶች ለማወያየት ጥያቄ አቅርበው ነው 11ዱ መመረጣቸው ተነግሯል።

የብዙሀን መገናኛ ተቋማት የሚያዘጋጁት ክርክር  የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከሚደለደለው የቅስቀሳ ሰዓት ጋር የሚገናኝ አይደለም ተብሏል ።

ድርጅቶቹም÷

1 ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

2 አሃዱ ቴሌቪዥን

3 ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ

4 ሴታዊት ሙቭመንት

5 የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች

6 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ

7 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት

8 ኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲሴብሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን

9 የኢትዮጵያ መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች ማህበር

10 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን

11 ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ናቸው።

ፓርቲዎች ከተመረጡት ውጭ  ያሉ ድርጅቶች በሚያዘጋጁት መድረኮች ላይ ተገኝተው የመሳተፍና የመከራከር መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን  ቦርዱ አስታውሷል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top