Connect with us

የፌደራል ዳኞች የመኖርያ ቤት ችግር እየተቀረፈ ነው

የፌደራል ዳኞች የመኖርያ ቤት ችግር እየተቀረፈ ነው
ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ዜና

የፌደራል ዳኞች የመኖርያ ቤት ችግር እየተቀረፈ ነው

የፌደራል ዳኞች የመኖርያ ቤት ችግር እየተቀረፈ ነው

የፌደራል ፍ/ቤት ዳኞችን የዳኝነት ነጻነት ከማንኛውም ውጫዊና ውስጣዊ ተጽዕኖዎች ነጻ በማድረግ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ከሚያስፈልጉ አቅርቦቶች መካከል መኖሪያ ቤት አንዱ መሆኑን ይታመናል፡፡ ከመንግሥት በተፈቀደ 750 ሚሊዮን ብር በጀት ፍ/ቤቱ ያስገነባቸው መኖሪያ ቤቶች ደረጃ በደረጃ ለዳኞች በዕጣ እየተላለፉ ይገኛሉ፡፡  

በዚህ መሠረት የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ከሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ባፀደቀው የፌደራል ፍ/ቤቶች ዳኞች የመኖሪያ ቤት አስተዳደር እና አጠቃቀም መመሪያ መሠረት በተቋቋመ ኮሚቴ አማካኝነት በቅርቡ ግንባታቸዉ የተጠናቀቁና መሰረተ ልማት የተሟላላቸዉ 32 የመኖሪያ ቤቶችን ለዳኞች አስተላልፏል፡፡

በተመሳሳይ ቀደም ሲል ግንባታቸው የተጠናቀቁ 80 የመኖሪያ ቤቶች በሐምሌ 2012 ዓ.ም ለዳኞች በዕጣ መከፋፈላቸው ይታወሳል፡፡

ቀሪዎቹን 166 የመኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ዝግጁ ለማድረግ የማጠናቀቂያ ስራ (Finishing work) ከሞላ ጎደል ያለቀለቸው ሲሆን ዕድሉን ለሚጠባበቁ ቤት ፈላጊ ዳኞች ለማስተላለፍ በዋናነት ለህንጻዎቹ የመወጣጫ አሳንሰር (Elevator) አለመገጠሙ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱ ታውቋል፡፡

የመወጣጫ አሳንሰሮቹን ለማስገጠም የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተግዳሮት ሆኖ የቆየ ቢሆንም ችግሩን ለመፍታት የሚመለከታቸው የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር በተደረገ ውይይት እና በወሰዱት መልካም እርምጃ አሳንሰሮቹን ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

የጋራ መኖሪያ ሕንጻዎቹ ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ የተገጠሙላቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረት ልማቶች የተዘረጉላቸው ሲሆን 278ቱ መኖሪያ ቤቶች እያንዳንዳቸው 18 ወለል ባላቸው አራት ህንጻዎች ላይ የተገነቡ ናቸው፡፡

ህንጻዎቹ ከያዟቸው መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 138 ቤቶች 121 ካ.ሜ ስፋት ያላቸው ባለሁለት መኝታ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 140 ቤቶች ደግሞ 147 ካ.ሜ ስፋት ያላቸው ባለሶስት መኝታ ክፍል ቤቶች ናቸው፡፡

የፌደራል ዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት ለማስጠበቅ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ሲደረጉ ከቆዩ ጥረቶች መካከል ለሥራና ለመኖሪያ ምቹ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለዳኞች የማስተላለፍ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራበትና ክትትል ሲደረግበት እንደነበር ይታወቃል፡፡

የሕንጻው ግንባታ በቀድሞ የፍ/ቤት አመራሮች የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አዲሱ የፍ/ቤት አመራር ሃላፊነት በወሰደበት ጊዜ የሕንጻው ግንባታ ሂደት ተስተጓጉሎ የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ በቀጥታ በግንባታ ውስጥ ሚና ባይኖረውም ኮንትራክተሩን፣ ተቆጣጣሪ መ/ቤቱን፣ የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስቴርን እንዲሁም ብሔራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይት በማደረግ ችግሮቹ በየደረጃው ተፈትተው የዛሬው ውጤት ተገኝቷል፡፡

ፍ/ቤቱ በዚህ ሂደት ውስጥ ሳይሰላቹ ሃላፊነታቸውን ለተወጡት አካላት ሁሉ ምስጋና ያቀርባል፡፡ በፍ/ቤቶቻችን በኩል የተወሰኑ ውሳኔዎች ወደ ተግባር እንዲለወጡና ተገቢውን ክትትል በማድረግ የውሃ እና መብራት አቅርቦት ተሟልቶ ዳኞች እጅ ቁልፍ እንዲገባ በማድረግ ረገድ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያደረገው ከፍተኛ ጥራት እውቅና ሊሰጠው ይገባል፡፡

(ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top