Connect with us

“ቤታችንን ሳንረከብ ሁለት ዓመት ሞላን” የ 40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች 

"ዕጣ ቢወጣልንም ቤታችንን ሳንረከብ ሁለት ዓመት ሞላን" የ 40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

ማህበራዊ

“ቤታችንን ሳንረከብ ሁለት ዓመት ሞላን” የ 40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች 

“ዕጣ ቢወጣልንም ቤታችንን ሳንረከብ ሁለት ዓመት ሞላን” የ  ዕድለኞች 

የ40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ወጥቶላቸው ቤቱን ሳይረከቡ ሁለት አመት እንደሞላቸው ቅሬታ አቅራቢዎች ተናገሩ።

ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅሬታ ይዘው ከቀረቡት ውስጥ የ2011 ዓ.ም የቱሪስት እና ሰሚት የጋራ መኖሪያ ቤት ሳይት እጣ የወጣላቸው ነዋሪዎች ይገኙበታል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ውል በገቡት መሰረት ቤቱን ባለመረከባቸው ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውን በመጥቀስ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉም ይጠይቃሉ።

አቶ ግርማ ላቀው በተጠቀሰው አመት በቱሪሰት የቤት እጣ እንደወጣላቸው ሲነገራቸው የነበራቸው ተስፋ እና ደስታ አሁን እንደሌለ ይናገራሉ።

እጣ እንደወጣለት ውል ፈፅሞ ወደ ቤት መግባት ተስፋ አድርገው የነበሩት አቶ ላቀው እንዳሰቡት አልሆነላቸውም።

አቶ ዳግም አይቸውም በሰሚት የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ወጥቶላቸው  ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ጋር ውል ቢፈፅሙም ቤታቸውን ግን መረከብ አልቻሉም።

እነሱን ጨምሮ በሁለቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጥቶላቸው ውል የፈፀሙ ቅሬታ አቅራቢዎች ቤታቸውን መረከብ እንዳልቻሉ ነው የሚናገሩት።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት ሰሚት ላይ ብሎክ አንድ እና ሁለት፣ ቱሪስት ላይ ደግሞ ካሉት 11 ብሎኮች አብዛኛዎቹ ያልተጠናቀቁ ናቸው።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በቱሪስት የ40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባደረገው ቅኝት ቤቶቹ እንዳልተጠናቀቁ እና ብዙ ስራ እንደሚቀራቸው መታዘብ ችሏል።

በሳይቱ የተወሰኑ ሰራተኞች በግንባታ ላይ ቢኖሩም በሙሉ አቅም ሙሉ ሰራተኞች እንዳልገቡም ነው በቅኝቱ የተረዳው።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ሰለሞን ዲባባ ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ጠቁመው በወቅቱ ማጠናቀቅ ያልተቻለው በበጀት እና የሰሚንቶ እጥረት መሆኑን ተናግረዋል።

ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅሬታ ለማቅረብ የመጡት የቱሪስት እና ሰሚት ሳይቶች ቢሆኑም በበሻሌ፣ ቦሌ ቡልቡላ እና ሌሎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይም ተመሳሳይ ችግሮች መኖራቸውንም ግለሰቦቹ ተናግረዋል።

ቃል በተገባላቸው ጊዜ እና ውል በተገባበት መሰረት ቤታቸውን መረከብ አለመቻላቸው ለተጨማሪ ወጪዳርጎናል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ አሁንም መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሚመለከተውን አካል ጠይቀዋል።

አስተዳደሩም ችግሮቹን መነሻ በማድረግ ከንግድ ባንክ ጋር በመነጋገር የአንድ አመት የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጣቸው መደረጉን አቶ ሰሎሞን ገልጸዋል።

አሁንም ቤቶቹን አጠናቆ ለማስረከብ እየተሰራ ነው ያሉት ሀላፊው ከሌሎች የመሰረተ ልማት ተቋማት ጋር በጋራ ኮሚቴ መዋቀሩን ጠቁመዋል።

ከተቋማቱ ጋር በቅንጅት መስራት ከተቻለም እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ቤቶቹን ለማጠናቀቅ ወደ ስራ ተገብቷልም ነው ያሉት።

ነዋሪዎቹ ባልተቀበሉት ፤ ችግራቸውንም ባልቀረፈ ቤት ዛሬም የባንክ ወለድ በተጨማሪ እየከፈሉ መኖር እንደተሳናቸው ገልጸዋል።(FBC)

 

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top