Connect with us

በአዲስ አበባ ሁለት የምሽት ቤቶች ተዘጉ

በአዲስ አበባ ሁለት የምሽት ቤቶች ተዘጉ
ኢትዮ ኤፍኤም

ዜና

በአዲስ አበባ ሁለት የምሽት ቤቶች ተዘጉ

በአዲስ አበባ ሁለት የምሽት ቤቶች ተዘጉ

በቦሌ የሚገኙት ታዋቂዎቹ ኤክሶ ኤክሶ እና በዕምነት የተሰኙት የምሽት ቤቶች በመንግስት ውሳኔ መታሸጋቸው ተገልጿል።

ከቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ጀርባ የሚገኙት ታዋቂዎቹ በዕምነት ባርና ሬስቶራንት ቁጥር 1 እና 2 እና XOXO የምሽት ክለብ በነዋሪዎች ቅሬታ ታሽገዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሚነኙ ነዋሪዎች በአካባቢው በሚገኙ ንግድ ቤቶች በተለይም በምሽት መዝናኛዎች ድምፅ ብክለትና ሌሎች ችግሮች መማረራቸውን ወረዳው ለጣቢያችን ተናግሯል።

ነዋሪዎቹ ከግሮሰሪ እስከ ማሳጅ ቤት በመኖሪያ ቤት አካባቢ መኖር በማይፈቀድላቸው ንግድ ቤቶች ተማረው ፤ ቅሬታቸውን ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ አቅርበዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አልባስ ሀይሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በመኖርያ አካባቢ ለምን ፍቃድ ተሰጠ የሚለውን ክ/ከተማው ስለሚያይ ነዋሪዎቹን ወደዛ ልከናል ።

ድምፅ ብክለትን በተመለከተ ግን ፤ XO XO የምሽት ክለብና እና በእምነት ባርና ሬስቶራንት ከሚፈቀደው 45 ዴሲቤል በላይ ሆነው ስላገኘን ከተደጋጋሚ ምክርና ማስጠንቀቂያ በኋላ ባለመስማታቸው ትናንት አሽገንባቸዋል ብለዋል።

የምሽት ክለቦቹ ከት/ቤት ምን ያህል መራቅ አለባቸው? ከቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር ባለ የንግድ ፍቃድ አሰጣጥ ጋር በተገናኘ፣ መዝናኛዎቹ ጋር የሚቆሙት መኪኖች ስለሚበዙ በፓርኪጉ ምክንያት መተላለፍ አለመቻላቸውን፣ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ነዋሪዎች  ቅሬታ  አቅርበዋል ብለዋል ሀላፊዋ።

እኛ በወረዳ ደረጃ የሚመለከተውን እንፈፅማለን፣ በዚህም መሰረት ሁለቱን ቤቶች በድምፅ ብክለት ምክንያት አሸገናቸዋል ሲሉ ነግረውናል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በአቂቃ ቃሊቲ ክፍል ከተማ የሚገኙት 11 መጠጥ ቤቶች ከተፈቀደዉ 45 ዴስባል የድምፅ መጠን በላይ አልፍዉ እሰከ 85 ዴሲባል መጠን ሲጠቀሙ በመገኝታቸዉ መታሸጋቸው መገለፁ የሚታወስ ነው።

ከዚራ ባርና ሬስቶራንት፣ ሰለሞን ጀርመን ሀዉስ ፣ ፋልከን ላወንጂ፣ ሴራኒ ባርና ሬስቶራንት፣ አዲናስ ባርና ሬስቶራንት ፣ ዊንግ ላዉንጂ፣ፋድ ዞን፣ ኤልቢስ ትሮ ባርና ሬስቶራንት ፣ሚሚስ አዲስ ባርና ሬስቶራንት፣ ሮያል ባርና ሬስቶራንት እንዲሁም ተክላኋይማኖት ግሮሰሪ መታሸጋቸው ተገልፆ ነበር፡፡

ሆኖም ግን እንደ አካባቢ ጥበቃ ሀላፊዋ እንደ ወ/ሮ አልባስ ከሆነ መመርያው ክፍተት አለበት።

 በመጀመርያ ዙር የታሸገበት ከ 5 ቀን እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 5 ሺህ ብር ከፍሎ ይከፈትለታል፣ ለሁለተኛ ዙር መመርያውን ጥሶ ከተገኘ 25 ሺህ ብር ይቀጣል፣ ከዚህ በኋላ ለሶስተኛ ጊዜ መመርያውን ሲጥስ ከተገኘ ነው ንግድ ፍቃዱ የሚነጠቀው።

 በዛ ላይ ይሄ ሂደት የኮሚቴ ስራ ስለሆነ የራሱ ክፍተት አለው ብለዋል።

ህብረተሰቡ በሚኖርበት አካባቢ ብክለት የሚያደርሱ ተቋማትን በ6713 የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረስ እንደሚችል የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን መልዕክት አስተላልፈዋል።

(ኢትዮ ኤፍኤም)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top