Connect with us

ጠቅላዩን ምን ነካቸው? ሁለት የተጋጩ ጥሪዎች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ

ጠቅላዩን ምን ነካቸው? ሁለት የተጋጩ ጥሪዎች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጠቅላዩን ምን ነካቸው? ሁለት የተጋጩ ጥሪዎች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ

ጠቅላዩን ምን ነካቸው? ሁለት የተጋጩ ጥሪዎች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ

(ያሬድ ኃ/ማርያም – የሰብአዊ መብት ተሟጋች ) 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትንሽ ግራ መጋባት ወይም የተሳሳተ የህግ ምክር ሳይቀርብላቸው አልቀረም። ከዚህ በታች በተያያዙት እና በተከታታይ ቀናት በወጡት ሁለት ደብዳቤዎች እጅግ የሚቃረኑ ሃሳቦችን አንጸባርቀዋል። በማይካድራ የተፈጸመውን ሰቆቃ በተመለከተ ጉዳዩ  crimes against humanity ስለሆነ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ ገብቶ ድርጊቱን እንዲያወግዝ እና አጥፊዎቹን ለፍርድ ለማቅረብ እንዲተባበር ይጠይቃሉ።

November 24, PM Abiy Ahmed

“We call upon the international community to condemn these atrocious acts of crimes against humanity and its perpetrators in no uncertain terms. The Government will spare no effort in bringing the perpetrators to justice.”

በዛሬው ደብዳቤያቸው ደግሞ በትግራይ ያለው ግጭት ሕግ የማስከበር ጉዳይ ስለሆነ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እጁን ይሰብስብ፣ በውስጥ ጉዳያችንም አይግባ፣ ማናቸውም አይነት ጣልቃ ገብነት የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚዳፈር ስለሆነ በተባበሩት መንግስታት ቻርተር አንቀጽ 2(7) ላይ የተደነገገውን በአገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህን የጣሰ ነው የሚል ሙግት አንስተዋል። 

November 24, PM Abiy Ahmed

“A fundamental element of the international legal order is the principle of non-intervention in the internal affairs of sovereign states, which is enshrined in Article 2(7) of the Charter of the United Nations. … We reject any interference in our internal affairs. “

እነዚህ ሁለት ሃሳቦች እርስ በርስ የሚጋጩ ብቻ ሳይሆኑ በተለይም ጣልቃ አትግቡ የተባለበት መንገድ ትንሽ ግልጽነት የጎደለው ይመስላል። 

1ኛ/ የአለም አቀፉ ማህበረሰቡ ወያኔ የፈጸመችውን ወንጀል እንዲያወግዝ መጥራት ማለት ኑና ነገሩን አጣርታችው እና መርምራችሁ አቋም ያዙ ብሎ መጋበዝን ይጨምራል። መቼም አለም አቀፉ ማህበረሰብ በእንዲህ ያሉ ጉዳዮች ላይ አቋም ለመያዝ የራሱ የአሰራር መንገድ እንዳለው ይታመናል። 

2ኛ/ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ግጭቱ በሚካሄድበት የትግራይ ክልል ውስጥ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ ቀውስ (humanitarian crisis) ያሳስበኛል በሚል የመፍትሔ ሃሳቦችን ሲያቀር ደግሞ አርፋችው ተቀመጡ ይሄ የውስጥ ጉዳይ ነው ማለት ከላይ ከቀረበው ጥሪ ጋር ይጋጫል።

እንደ እኔ እምነት ጣልቃ ግቡ እና ጣልቃ አትግቡ ከሚሉ የተጋጩ ጥሪዎች ይልቅ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ባቀረባቸው ዝርዝር የመፍትሔ ጥሪ ሃሳቦች ላይ አንድ በአንድ አቋም ይዞ መነጋገር ይሻላል። ይሄን በፍጹም አንቀበልም፣ ይሄን እንቀበላለን ቢባል ጥሩ ነው።

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top