Connect with us

የመከላከያ ሚኒስትሩ ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ከሆኑ ወታደራዊ አታሼዎች ጋር መከሩ

የመከላከያ ሚኒስትሩ ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ከሆኑ ወታደራዊ አታሼዎች ጋር መከሩ
አዲስ ቲቪ

ዜና

የመከላከያ ሚኒስትሩ ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ከሆኑ ወታደራዊ አታሼዎች ጋር መከሩ

የመከላከያ ሚኒስትሩ ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ከሆኑ ወታደራዊ አታሼዎች ጋር መከሩ

የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀነዓ ያደታ፣ ጽንፈኛው የህወሃት ቡድን የብሔር ግጭቶች ማስነሳቱን፣ ብዙ ህዝብ እንዲጨፈጨፍ ማድረጉን፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት መጣሱን፣ ጦርነቱንም ራሱ ሰሜን እዝን በማጥቃት እንደጀመረው እና ኢትዮጵያም የህግ የበላይነት እያስከበረች መሆኗን ተቀማጭነታቸውን ኢትዮጵያ ላደረጉ ወታደራዊ አታሼዎች ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ቀነዓ ነጻ በወጡ አካባቢዎች መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ኢትዮጵያ የውጭ ድጋፍ የምትፈልግበት ምንም ምክንያት እንደሌለ እንዲሁም ሠራዊቱ የጦርነት ህግና የዓለም ዓቀፍ ህግን እንደሚያከብር አረጋግጠዋል።

በውይይቱ ላይ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀ አስራት ዴኔሮ፣ ጁንታው ህገ መንግስቱን ጥሶ የፈፀመውን ግድያ፣ የሰላም መንገድን ረግጦ ሰሜን እዝን በመውረር ግጭቱን እንዴት እንደ ጀመረው፣ እያሰራጨ ስላለው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ህግን ለማስከበር እያደረገ ስላለው ጥረት በዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰብዓዊ ድጋፍ፣ በውጭ ጣልቃ ገብነትና በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላነሱት ጥያቄ የመከላከያ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመኮንኖች ክበብ በተካሄደው በዚሁ መድረክ ላይ ከ45 አገራት የተውጣጡ 70 ወታደራዊ አታሼዎች መሳተፋቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።(አዲስ ቲቪ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top