Connect with us

ህወሓቶች ራስ ወዳዶች ስለሆኑ በሰላም እጃቸውን ይሰጣሉ ብለው እንደማይገምቱ  የሶማሌ ክልል  ም/ፕሬዚደንት ገለጹ

ህወሓቶች ራስ ወዳዶች ስለሆኑ በሰላም እጃቸውን ይሰጣሉ ብለው እንደማይገምቱ የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዚደንት ገለጹ
Photo: Social media

ዜና

ህወሓቶች ራስ ወዳዶች ስለሆኑ በሰላም እጃቸውን ይሰጣሉ ብለው እንደማይገምቱ  የሶማሌ ክልል  ም/ፕሬዚደንት ገለጹ

ህወሓቶች ራስ ወዳዶች ስለሆኑ በሰላም እጃቸውን ይሰጣሉ ብለው እንደማይገምቱ  የሶማሌ ክልል  ም/ፕሬዚደንት ገለጹ

 

የህወሓት ጁንታ ቡድን ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለስ አረመኔ ድርጅት በመሆኑ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ መመሸጉ የሚያስገርም እንዳልሆነ  የገለጹት የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሃመድ ራስወዳዶች ስለሆኑ በሰላም እጃቸውን ይሰጣሉ ብለው እንደማይገምቱ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ  ትናንት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት፤ የጁንታው ቡድን አመራሮች በደም የጨቀዩ ፣ ምንም ከማድረግ የማይቆጠቡ ናቸው።

በመስኪድ፣ በቤተ ክርስቲያን አጸዶች ፣ በአዛውንቶች መጦሪያና የህፃናት ማቆያ ጭምር የከፋ ጭፍጨፋ በማድረግ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሊሞክሩ እንደሚችሉ ያመለከቱት አቶ ሙስጠፋ፣ ህግ የማስከበር እርምጃው ሌላ አቅጣጫ እንዲይዝ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው መጠለላቸው የሚገርም እንዳልሆነ አስታውቀዋል። በዚያ ከመመሸግ ባሻገር እራሳቸው ቤተክርስቲያኑን ሊያጋዩ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችልም ጠቁመዋል ።

ከቅርብ ግዜ ታሪክ እንደምንረዳው ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ሆቴሎችን ሳይቀር እራሳቸው በቦምብ በማጋየት በሌላ ድርጅት ላይ ጣታቸውን ሲጠቁሙ እንደነበር ያመለከቱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ፈጥኖ ማጠናቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

“የከሀዲው ህወሓት ቡድን አመራሮች እጅ አንሰጥም የሚሉት መጨረሻ ይታያል። ከታሪክ እንደምንረዳው ወጣቶችን እያስጨፈጨፉ በእነሱ ተገን ሆነው ስልጣን ላይ የሚቀጥሉ አምባገነኖች በመጨረሻ ሰዓት ላይ ባልተጠበቀ ሁኔታ እጅ ሲሰጡ፤ ባሳፋሪ ሁኔታ ሽንፈት ሲቀበሉ የታየበት የታሪክ አጋጣሚዎች አሉ”ብለዋል ።

በመቀሌ ላይ ድል እናደርጋለን በሚል ተስፋ ለማያሸንፉት ጦርነት ህዝቡን ለጥፋት ከሚዳርጉት በሰላም እጃቸውን ቢሰጡ የተሻለ ነው ያሉት አቶ ሙስጠፌ፣ እጅግ ሲበዛ እራስ ወዳድ በመሆናቸው ያደርጋሉ ተብሎ ግን እንደማይታሰብ አመልክተዋል።

‹‹ህግ የማስከበር ኦፕሬሽኑ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። አብዛኛው አካባቢ ነፃ ወጥቷል። የቀሩት ደግሞ በቅርቡ ነፃ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል›› ያሉት አቶ ሙስጠፋ፤ የሱማሌ ክልል ህዝብና መንግስት የሚካሄደውን ህግ የማስከበር ሂደት እየደገፈ ይገኛል ብለዋል።

ወንጀለኛ ቡድኑን በቅርቡ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ለፈፀመው አሳፋሪ ጥቃትና በተለያዩ አካባቢዎች በብሄርና በሃይማኖት የማጋጨት ወንጀሎች በሙሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ከፌዴራል መንግስት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ሽንፈቱን መቀበል ያቃተው ጁንታው ቡድን የመሰረተ ልማት አውታሮችን ማውደም መጀመሩን የጠቆሙት የክልሉ ም/ፕሬዚዳንት ፣ይህ አይነት እኩይ ተግባር ለቡድኑ አዲስ አለመሆኑ ጠቁመዋል። በታሪክ እንደሰፈረው ትግል ጀምሬያለሁ ካለበት ጊዜ አንስቶ ሲፈፅመው የነበረ ተግባሩ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ባጠቃላይ ቡድኑ 50 ዓመት ለሚሞላ ጊዜ የትግራይን ህዝብ የተለያዩ አጀንዳዎች በመስጠት አንድ ጊዜ ‹‹ተጨቁነሀል›› በሌላ ግዜ ደግሞ ‹‹በሌሎች ላይ የበላይነት ይኖርሃል›› እንዲሁም ‹‹ልትጠቃ ነው›› የሚል ቅስቀሳዎችን እያደረገ ወጣቶችን ወደ ጦርነት በመክተት እያስጨፈጨፈ ቆይቷል። ህዝቡም ሰላም እንዳያገኝ ሲሰራ ኖሯል። በመሆኑም ከማንም በላይ ይህ ቡድን መወገዱ የሚጠቅመው ለትግራይ ህዝብ መሆኑን ተናግረዋል።

‹‹ህዝቡ የሰላም አየር አግኝቶ ከቀሪው ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በእኩልነት የሚኖርበት ቀን በቅርብ ግዜ ውስጥ ይመጣል። እንደ ድሮውም ጫካ ለጫካ እየዞሩ የሚመጣ ድል የለም›› ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ፤ ትግል አላማ ሲኖረው እንጂ ለበላይነትና ሌሎችን ሰላም ለመንሳት ከሆነ አይሳካም ብለዋል። የትግራይ ህዝብም ይሄ አካሄድም የሚጠቅም ባለመሆኑ ከትህነግ እኩይ አላማ በተቃራኒ ሊቆም እንደሚገባም አመልክተዋል።

እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለፃ፤ የጁንታው የህወሓት ቡድን በቀጥታ ግንባር ላይ ከመዋጋት ባሻገር በሌሎች ክልሎች ውስጥ ሰላም እንዳይኖርና ይሰራል። ከዚህ ቀደምም የአብዲ ኤሊን አስተዳደር በመጠቀም በኦሮሚያና የሱማሌ ክልል መካከል ግጭት እንዲፈጠር፤ የሃይማኖት ሁከት እንዲነሳ በአጠቃላይ በምስራቅ ኢትዮጵያ ቀውስ እንዲፈጠር ሲሰራ ቆይቷል። ይህ እኩይ አላማ እንዲከሽፍ በተደረገው ፈጣን የአስተዳደርና የፀጥታ መዋቅር ማስተካከያና ህዝቡ ከክልሉ የለውጥ ሃይል ከጎን በመቆሙ ሳይሳካ ቀርቷል።

የክልሉ መንግስት ከኬኒያ እስከ ጅቡቲ እንዲሁም እስከ ሶማሊያ ድረስ ሰፊ ድንበር በልዩ ሃይሉ የመጠበቅ ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ ነው። አሁን ላይ በአካባቢው ያለው የጁንታው ኔትወርክ ተበጣጥሷል። እረብሻና ሁከት ለመፍጠር መሞከራቸው ግን አንድም ቀን አቁመው አያውቁም። በዚህ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በደቡብ፣ በቤኒሻንጉልና በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ግድያዎችን እየፈፀሙ ዜጎች በለውጡ ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ ለማድረግ እየሚከሩ ነው። በመሆኑም መላው ኢትዮጵያዊ ይሄን እኩይ ተግባር በተባበረ ክንድ በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያስወግድ ያላቸውን ከፍ ያለ ተስፋ ገልጸዋል ።

(አዲስ ዘመን ህዳር 11/2013)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top