Connect with us

ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ማን ናቸው?

ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ማን ናቸው?
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ማን ናቸው?

ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ማን ናቸው?

ጀነራሉ ምሁር ናቸው፡፡ የተማረው ወታደራዊ ሳይንስ ብቻ አይደለም፡፡ የመጀምሪያ ዲግሪያቸው ህግ (LLB) ነው:: ድንቅ ውጤት በማምጣት የተመረቁ ናቸው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት በአመራር ሳይንስ ላይ ነው፡፡ በሰራባቸው ቦታዎች ሁሉ ውጤታማ ናቸው ምክንያቱም የሚሰጡት አመራር ተለምዶአዊ ሳይሆን በእውቀት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

ለውጥ ይወዳል፡፡ ይህ በወታደሩ ዘንድ በደንብ ይታወቃል፡፡ የሆነ ነገር ለውጥ ሲያስፈልገው እስቲ ባጫ እዚያ ማእከል/ዕዝ አንድ ጊዜ አይቶ ይምጣ ይባላል፡፡

ሁሌ ወጣት ነው ምክንያቱም ስፖርት መስራት ባህሉ ነው፡፡ በመሆኑም እርጅና የሚባል ነገር አይነካውም፡፡ ጀነራሉ አይፈራም፣ ቤቱ ለሁሉም ክፍት ነው፣ ግልፅ ነው፣ ተናግሮ ያሳምናል፣ ለሱ ሁሉም እኩል ናቸው (ትልቅ፣ ትንሽ፣ ሀብታም፣ ደሃ፣ የተማረ፣ ያልተማረ፣ ነጋዴ፣ አ/አደር ወዘተ)፡፡ ከዚህም የተነሳ ማንም ሰው ይወደዋል፡፡ አሁን በተፈጠረው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከጥንትም ጀምሮ ነው የሚወደደውና የሚደነቀው፡፡  የጎለ-ኦዳ፣ ቡርቃ፣ በደኖ፣ መዩ፣ የባሌና የጅማ ወረዳዎች ወዘተ ነዋሪዎች ምስክር ናቸው፡፡

ከዚህም የተነሳ ባለፉት ዓመታት የሚፈሩም አልጠፉም፡፡ ያለ እድሜው በጡረታ አገለሉት፡፡ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ገና ብዙ ይሰራል፡፡ አገር ወዳድ የሆናችሁ ሁሉ እናበረታታው፤ እንደግፈው፣ ሞራል እንስጠው።

ኢትዮጵያ ብዙ ጀግኖች አሏት! በዚህ አጋጣሚ፣ በቅርብ ግዜ ከዶክተር አብይ የናት አገር ጥሪ የተቀበሉ ጀግኖች ሌ/ጀኔራል አበባው ታደሰ እና ሌ/ጀኔራል ባጫ ደበሌ አገራችሁን ስለምታገለግሉ በጣም እናመሰግናችኋለን! እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች! እግዚአብሔር ሰላም ለአገራችን ያምጣልን!።” Umer Sheni

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top