Connect with us

“በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ  የሚታየው ቸልተኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል” የሃይማኖት አባቶች 

"በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚታየው ቸልተኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳደር ይችላል" የሃይማኖት አባቶች
ትምህርት ሚ/ር

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

“በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ  የሚታየው ቸልተኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል” የሃይማኖት አባቶች 

“በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ  የሚታየው ቸልተኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል” የሃይማኖት አባቶች 

 

ትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስትቲዩት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት በማስቀጠል ሂደት ላይ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ሲያደርጉት የነበረው ምክክር ተጠናቋል።

በምክክር መድረኩ የሃይማኖት አባቶቹ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የመንግስትና የህዝብ ቸልተኝነት እያታየ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ ቸልተኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር ስጋታቸውን ገልፀዋል።

መንግስት ኮሮናን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎች እንዲተገበሩ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ የጠየቁት የሃይማኖት አባቶቹ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ህብረተሰቡን በማንቃት የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

መንግስት ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲከላከል ከማስተማር ባለፈ አስገዳጅ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተገለጧል። 

ተማሪዎችም በትምህርት ቆይታቸውም ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ተብሏል።(ትምህርት ሚ/ር)

 

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top