Connect with us

ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

በዛሬው ዕለት ከህወሃት የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በጋምቤላ ክልል ብሄር ብሄረሰቦችን ለማጋጨት አሲረው ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል የተጠረጠሩ ጸጋዬ መብርሃቱ (ካህሳይ)፣ ገብረ ማሪያም አናንያ ፣ዋስትና ተሾመ (ጃል ሴና)፣ አብርሃም መሃሪ፣ ኮሎኔል ተስፋዬ (ባሌስትራ) እና ሌሎች 19 የህወሃትና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤

በክልሉ ብሄር ብሄረሰቦችን በማጋጨት አካባቢውን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ አሲረውት የነበረው ሴራ ከሽፏል፤ ግለሰቦቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በተመሳሳይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ተፈጽሞ የነበረ ተመሳሳይ ጥፋት በዚያው በክልሉ ውስጥ በአሶሳና ካማሼ ዞኖች ብሔር ብሄረሰቦችን በማጋጨት አካበቢውን የትርምስ ቀጠና በማድረግ እልቂት ለመፈጸም የህወሃት የጥፋት ቡድን አባል ከሆነው አባይ ጸሃዬ ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ዮሃንስ ግርማይና ርዕሶም ግርማይ ከሌሎች 20 ግብረ አበሮቻቸው ጋር በቁጥር ስር ውለዋል፤

በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እነዚህን የጥፋት ሃይሎች በቁጥጥር ስር ለማዋልና ሴራቸውን ለማክሸፍ በተፈጸመ ኦፐሬሽን የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የየክልሎቹ የጸጥታ አካላት በቅንጅት ተሳትፈዋል።

በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ጥፋት ለመፈጸም ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የጥፋት ሃይሎች ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው።

አጠቃላይ የጥፋት ሴራውን በማክሸፍ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ በተከታታይ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top