Connect with us

ይድረስ ለጠ/ሚኒስትሬ!

ይድረስ ለጠ/ሚኒስትሬ!
Photo: Social media

ዜና

ይድረስ ለጠ/ሚኒስትሬ!

ይድረስ ለጠ/ሚኒስትሬ!

የለውጥ አመራሩ ተገዶ ጦርነት ውስጥ ገብቷል። የሚዋጋው በሙስና፣ በብልሹ አሰራርና በሴራ ከተካነ የዘራፊዎች ስብስብ ጋር ነው። ይኸ ስብስብ በሐሰት ትርክት ለአመታት ሕዝብን ጭምር የማደናገር አቅም የገነባ ነው። በሴራ እና በመከፋፈል አካሄድ እስትንፋሱን ለአመታት ማስቀጠል የቻለ ነው። በኘሮፖጋንዳም የበላይነት ለመቀዳጀት ተከፋይ የፌስቡክ አርበኞችን፣ አንዳንድ ጋዜጠኞችና ሚድያዎችን ጭምር ሲቀልብ የኖረ ነው። 

 እናም ህዝብ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ፈጣን መረጃ ማቅረብ የግድ ይላል።እንደኔ እንደኔ አንድ ቃል አቀባይ ቢሮ በፍጥነት ተደራጅቶ  በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ በአገር ውስጥና በውጭ ቋንቋዎች መረጃዎችን ለሚድያዎች እንዲሰጥ ቢደረግ የተሻለ ውጤት ይኖረዋል እላለሁ። የፈጣንና ትክክለኛ  መረጃ ስርጭት መኖር በተለይ የሐሰተኛ መረጃና አሉባልታዎችን ለመዋጋት ብቸኛ መንገድ ነውና ቢታሰብበት?!

(ጫሊ በላይነህ)

 

ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ጥሪ

“ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው። ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።

 መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል። ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም። 

የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል።  ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።”

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች  በንቃት እንዲቃኝና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top