Connect with us

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ወደ ብሔራዊ ፓርክ ለማሳደግ ታቅዷል

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ወደ ብሔራዊ ፓርክ ለማሳደግ ታቅዷል
የመረጃ ምንጭ አቶ አብርሃም ማርዬ

መዝናኛ

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ወደ ብሔራዊ ፓርክ ለማሳደግ ታቅዷል

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ወደ ብሔራዊ ፓርክ ለማሳደግ ታቅዷል

የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለለስልጣን በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ወደ ብሔራዊ ፓርክ ለማሳደግ የክለላና መረጃ ማጠናቀር ስራ ጀመረ።

ማራኪዉን የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ወደ ብሄራዊ ፓርክ ለማሳደግ ክለላና መረጃዎችን የማጠናቀር ስራ ከጥቅምት 16 ቀን 2013 ጀምሮ እየተካሄደ ነዉ፡፡

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ጥብቅ ደን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በባሶና ወራና፤በአንኮበርና በጣርማበር ወረዳዎች ይገኛል፡፡

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ከደብረ ብርሃን ከተማ 24ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከደብረብርሃን ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 39042’00’’ እስከ 39040’00″ ምስራቅ ሎንግቲውድና ከ9034’00″ እስከ 10020’00” ሰሜን ላቲቲዩድ ላይ ይገኛል፡፡የወፍ ዋሻ ደን የመሬት አቀማመጥ በጣም ወጣ ገባ ሲሆን 55% ዳገታማ 35% ወጣ ገባ እና 5% ሜዳማና 5% አምባ ነው (SUNARMA,2002) በባለስልጣኑ ባለሙያዎች አቶ አብርሃም ማርዬ እና አቶ አበጀ ዘዉዴ በ2010/2002 ባጠኑት ጥናት መሰረት በአፄ ዘርዓያቆብ ዘመነ መንገስት፡- የወፍ ዋሻ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን አጠባበቅ ትሩፋት በኢትዮጵያ ታሪክ በደንና ዱር እንሰሳት ጥበቃ ፋና ወጊ አፄ ዘርዓያቆብ 15ኛው ክፍለ ዘመን ይወስደናል፡፡

በአፄ ዘርዓያቆብ በኢትዮጵያ ነገስታት ታሪክ እንደዛሬው የደን መመናመን በአለም አቀፍና በሃገር ደረጃ ያመጣው ጉዳት ሳይታወቅ እንዲሁም ደግሞ አገሪቱ ከ70% (Tadesse Woldemariam et al., 2000; Million Bekele, 2001) በላይ በደን በተሸፈነችበት፤ ጥቅሙም በወቅቱ እምብዛም ጐልቶ በማይታዎቅበትና ዘመናዊ ትምህርት በማይሰጥበት ወቅት ነዉ፡፡ ለመናገሻ ሱባ ፣ ለወፍ ዋሻ ፣ ለደንቆሮ ጫካና ለስሜን ተራራዎች የሰጡት የጥበቃ ትኩረት በአገር ብቻ ሳይሆን በአፍሪቃም የደን ተቆርቋሪ እንደሆኑና ዛሬ ለሚደረገዉ የጥበቃ ሂደት መሰረት ጥለዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት የወፍዋሻ ደን ከአፄ ዘርዓያቆብ ጀምሮ ሲጠበቅና በኋላም በ18ኛው ክፍል ዘመን መሪ ደጃዝማች አምሃ እየሱስ /1744-1775/ የአንኮበርን ለሸዋ መናገሻነት በመመስረትና ለደኑ ጥበቃ በሰጡት ትኩረት በስፋት የደኑን ማዕከላዊ ክፍል ሸፍኖ የሚገኘው የአበሻ ጽድ የአምሃ እየሱስ ጽድ በመባል እስካሁንም እሳቸው እንደተከሉት ተደርጎ ይነገራል፡፡

በአጼ ሚኒሊክ ዘመነመንግስት ጀምሮ የወፍ ዋሻ የንጉስ ደን ከመባል ወደ መንግስት ደን ሲሸጋገር በጥበቃ ለተሠማሩት ዘበኞች በሪም (በደኑ አቅራቢያ ካሉ የእርሻ መሬት ተለይቶ ሕዝብ እንዲያርስላቸውና በምርቱ) እንዲተዳደሩ ተፈቀደ፡፡

በአፄ ሐይለስላሴ ዘመነ መንግስት በጣርማ በር ወረዳ በ1850ቹ የተቋቋመዉ የወፍ ዋሻና ሙገሬ ዛላ ደን ጽ/ቤት በተገኘው መረጃ መሰረት በ1890 ዓ.ም የተወለዱትና አስከ 1954 ዓ.ም ድረስ በሪም ይጠብቁ የነበሩት አቶ ቸርነት ወልደ አማኑኤል በ1950ቹ ዘጠኝ ቋሚ ዘበኞች ጋር በደመወዝ እንዲቀጠሩ ተደረገ።

በደርግ ዘመነ መንግስት ከ1967-1983) የዎፍ መንግስት ከፍተኛ ደን ተብሎ ጥበቃዉ ተጠናክሮ የችግኝ ጣቢዉ ደረጃዉን በማሻሻል የአገር በቀል ዘፎችን ጨምሮ በዙሪያዉ ጥቅም ሰጭ ሰዉ ሰራሽ ደን በሰፋት በመትክል በተጠናከረ ሁኔታ ይጠበቅ ነበር፡፡

የስነምህዳር ውክልና የወፍ ዋሻ ደን በተለያዩ ምክንያቶች እየተመናመነ ቢመጣም በጣም ማራኪ የሆኑ የስነ ምህዳር አምባ ነው፡፡

በአቀማመጡ የደጋማውን ከፍተኛ አካባቢ ከደበሌ እስከ ባሶ ደንጎራ የአፍሮ አልፓይን ገጽታና እጽዋት እንደ ጅብራ አስታ፣ ጓሣ ፣ የዋሊያ ሾህ (ጋርዳ)፤ ጦስኝ፤ የደጋ አሸንዳ /የጅብ ሸኅንኩርት/ የሚበቅሉበት በዋነኛነት ሜዳማና ከዋናው ደን ቀጥ ባሉ
ገደል የተከፈለ ነው፡፡ የገደሉን አፋፍና ግርጌ ተጠንተው እስከ 15ዐ ሴ.ሜትር ዲ.ቢ.ኤች በላይ ባላቸው ግዙፍ የሀበሻ ጽድ፤ ዝገባ ፤ ኮሶ፤ ወይራ፤ ዛፎች የተሸፈነ ነዉ፡፡

ዝቅተኛና ሸለቋማ የሆነዉ ሞንታኒ ደን ከጅረቶች መነሻ ጀምሮ እስከ ዋዲወንዝ ድረስ አብዛኛውን ቦታ የሸፈነ የሃበሻ ጽድ፤ ቀጨሞ ፣ ወይራ ፣ ምሣር ገንፎ ፣ ወይል ፣አምጃ ኮሶ ፣ አዛምር ፣እምብስ ፣ ቀለዋና ወይናግፍት የሚባሉ እጽዋቶች ይገኛሉ፡፡

ዱር እንሰሳት በአሁኑ ሰዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚታወቁት ተራ ቀበሮ፣ የደልጋ አንበሳ፣ ጦጣ ጥርኝ ፤ ጉሬዛ ፣ ነጠብጣም ጅም ፣ ባለመስመር ጅብ ፣ ጃርት ፣ የስታርክ ጥንቸል ፣ ሰሳ ፣ ጭላዳ ዝንጅሮ ፣ ሽክኮ፣ ተራና የሚኒሊክ ድኩላ ጥቂቶቹ ናቸው።

የአእዋፍ ዝርያዎች ከኤርትራ ጋር የምንጋሪቸው ዋትልድ አይቤስ፤ ኋይት ኮላር ፒጐን ፣ ብላከ ውይንግድ ላቨበርድ፣ ቲክ ቢልድ ሪቨን፣ ኋይት ቢልድ ስታርሊንግ ፣ብሉ ወይንግድ ጉዝ እና ክሊፍ ቻት ሲሆኑ በአገራችን ብቻ የሚገኙ ደግሞ አንኮበር ሶሪን እና አብሲኒያን ሎንግ ክላው ናቸው፡፡

በመሆኑም በመሬት አቀማማጡ ማራኪ፤ አገር በቀልና ብርቅየ አጥቢዎች፤ አእዋፋትና አጽዋት የያዘና ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረዉን የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ወደ ብሄራዊ ፓርክ በማሳደግና የቱሪዝም መሰረተ ልማቱን በማስፋፋት ወደ ተሻለ የጥበቃ ትኩረትና ጥቅም ለማሻሻል ከ16/02/2013 ጀምሮ የባለስልጣኑን የክልል ባለሙያዎችጨምሮ አስከ ቀበሌ ድረስ የሚገኙ የሚመለከታቸዉ ባላሙያዎች፤ ህብረተሰቡና ባላድርሻ አካላት የክለላና መረጃ የማሰባሰብ ስራዎችን እያከናዎኑ ይገኛሉ፡፡

የመረጃ ምንጭ አቶ አብርሃም ማርዬ ( የባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ዳይሬክተርና የጥናቱ አስተባባሪ)

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top