Connect with us

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከአገልግሎት ታገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከአገልግሎት ታገደ
ኢትዮ ኤፍ ኤም

ዜና

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከአገልግሎት ታገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከአገልግሎት ታገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የኮሮና ቫይረስ የደህንነት መስፈርት ባለማሟላቱ ለአገልግሎት ክፍት እንዳይሆን መታገዱ ተሰማ።

የቲያትር ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ከፈለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ህዳር መጀመሪያ ላይ የቴአትር ቤቱን 65ኛ አመት አስመልክቶ ለአገልግሎት ክፍት ልናደርግ ነበር ብለዋል፡፡

ነገር ግን ከጤና ጥበቃ ሚንስቴር መጥተው በጎበኙበት ወቅት ትያተር ቤቱ የጤና ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ፕሮቶኮሎችን ባለማሟላቱ በቅርቡ እንዳይከፈት ማዘዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ቴአትር ቤቱን ምቹ ለማድረግ ከረቡዕ ጀምሮ ጽዳት እንደሚጀመር ሰምተናል፡፡

ቴአትር ቤቱ ስራ ሲጀምር 3 ቴአትሮች የተመረጡ ሲሆን 10 ያልበለጡ ተዋናዮች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

በኮሮና ምክንያት ቴአትር ቤቱ በመዘጋቱ የቋሚ ተቀጣሪዎች ደሞዝ አልተቋረጠም ያሉት አቶ በፍቃዱ የተጋባዥ ተዋንያን ደሞዝ መቋረጡ እንዳሳሰባቸውም ተናግረዋል፡፡

ትያትር ቤቱ መች እንደሚከፈት በውል ያልታወቀው ሲሆን መስፈርቱን አሟልቶ ሲከፈት አዳራሹ ከሚችለው አንድ አራተኛው እንደተፈቀደለት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡

(ኢትዮ ኤፍ ኤም )

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top