Connect with us

“የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ሰላም ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ይሰጣቸው!” ኢዜማ 

"የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ሰላም ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ይሰጣቸው!" ኢዜማ
Photo: Social media

ዜና

“የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ሰላም ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ይሰጣቸው!” ኢዜማ 

“የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ሰላም ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ይሰጣቸው!” ኢዜማ 

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሰሞኑን በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በተፈፀሙ ጥቃቶች እና ግጭቶች ሕይወታቸው ባለፈ ኢትዮጵያዊያን ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል።

የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት በተደጋጋሚ ሲገረሰስ፣ ሚሊዮኖች ሕልውናቸው አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ መፈናቀል እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተደጋግሞ ሲከሰት መንግሥት ዋነኛ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት የሚችልበት ደረጃ ላይ የማይገኝ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ዜጎች ክቡር የሆነ ሕይወታቸውን ሲያጡ መመልከት የዕለት ተዕለት ዜና እየሆነ መጥቷል፡፡ጉዳዩ እየተደጋገመ ቢመጣም መንግሥት ግብታዊ መልስ ከመስጠት እና ጉብኝት ከማድረግ ባለፈ በዘላቂነት ችግሩን መፍታት እና የዜጎችን ከሁሉ በላይ መሰረታዊ የሆነውን በሕይወት የመቆየት መብት ማረጋገጥ አልቻለም፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በተደጋጋሚ ዜጎች ሕይወታቸው ሲቀጠፍ ተስተውሏል፡፡ በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የዜጎቻችንን ክቡር ሕይወት አጥተናል። ይሁን እንጂ መንግሥት ጉዳዩን የተመለከተበት እና ውሳኔ የሚያሳልፍበት መንገድ እጅግ የዘገየ፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት እና አስከፊነት ከግምት ያልከተተ ሆኖ ይታያል፡፡ 

በአጠቃላይ እነኝህ እየታዩ ያሉ ግድያዎች፣ ግጭቶች እና መፈናቀሎችን ከምንጫቸው ማድረቅ የሚቻለው ማንነት ላይ ያተኮረውን የሀገራችንን ፖለቲካ ለሁሉም ዜጎች እኩል ዕድል የሚሰጥ እና እኩል መብት የሚያከብር በዜግነት ላይ በተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስንቀይር እንደሆነ በፅኑ እናምናለን።

ይህን ማድረግ የሚቻልበት ሁሉንም የፖለቲካ አመለካከቶች ያሳተፈ እንዲሁም ሕዝብ የሚሳተፍባቸው ውይይቶች እስከሚደረጉ ድረስ የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት እና የሀገርን ሰላም እና ደህንነት መጠበቁ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሆኖ በትልቅ ትኩረት ሊከወን የተገባው መሆኑ ነው።

የዜጎች በሕይወት መኖር መሰረታዊ መብት ባልተከበረበት ሁኔታ በሕይወት ቆይተው ኑሯቸውን ለማሻሻል እና የነፃነት አድማሳቸውን ለማስፋት  የሚያስችሉ የልማት ሥራዎች ትርጉም ሊኖራቸው አይችልም።

 ኢዜማ ይህንን ጉዳይ በሁሉም የተደራጀባቸው ወረዳዎች በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በድርጊቱ ብዙዎች የሕይወት መስዋዕትነት በመክፈላቸው የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን፡፡ የድርጊቱ ፈጻሚዎች እና አስፈጻሚዎች ህግ ፊት ቀርበው ተገቢው ፍርድ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top