Connect with us

የህዳሴው ግድብ፣ የጸረ ፕ/ት ትራምፕ ተቃውሞው …

የህዳሴው ግድብ ፣ የጸረ ፕ/ት ትራምፕ ተቃውሞው ...
Secretary of State Mike Pompeo and White House senior adviser Jared Kushner applaud as U.S. President Donald Trump is on the phone with leaders of Israel and Sudan at the White House in Washington DC., Oct. 23.

አለም አቀፍ

የህዳሴው ግድብ፣ የጸረ ፕ/ት ትራምፕ ተቃውሞው …

የህዳሴው ግድብ ፣ የጸረ ፕ/ት ትራምፕ ተቃውሞው …
(ታምሩ ገዳ)

የአሜሪካው ፕ/ት ዶናል ትራምፕ በኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ድርድር ዙሪያ የስጡት “ፈር የለቀቀ “አነጋገር ከቅርብ አጋሮቻቸው ሳይቀር ብርቱ ዲፕሎማሲያዊ ትችት እና ተግሳጽ እየገጠማቸው ይገኛል።

ፕ/ት ትራምፕ “ግብጽ የህዳሴው ግድብን ልታጋየው ትችላለች” በማለት በትላንትናው እለት የሰጡት አስተያየትን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ጉዳይ ሹም የሆኑት ጆሴፍ ቦሪል በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲቀጥል ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን “በህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ጉዳይ ዙሪያ የተጀመረው ድርድር ወደ መስማምት ምእራፍ ላይ ደርሷል ” ያሉት የአውሮፓ ህብረቱ ከፍተኛ ሹሙ ጆሴፍ “በአሁኑ ወቅት የሚያስፈልገው ውጥረት ሳይሆን ወደ ድርጊት መግባት ነው” ብለዋል።

በመጨረሻም የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር እና የደ/አፍሪካ ፕ/ት በሆኑት ሲሪያል ራምፎዛ ሸምጋይነት፣በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ህብረት ፣በአለም ባንክ ታዛቢነት የተጀመረው እና ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ የተቋረጠው የሶስትዮሽ ድርድር ፍሬ እንዲያፈራ የአውሮፓ ህብረት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጠው ጆሴፍ ቦሪል የኮሚሽኑ አቋምን ገልጸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የፕ/ት ትራምፕን ” ያልተገራ” አነጋገርን በመቃወም የአሜሪካ ፖለቲከኞች ተቃውሟቸውን እና ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።ከእነዚህ ፓለቲከኞች መካከል በኮላራዶ ግዛት የዲሞክራት ፓርቲ የህዝብ እንደራሴ የሆኑት ጃአሶን ክሮው በትዊተር ገጻቸው ላይ ትራምፕን”ሀላፊነት የጎደላቸው፣ የአሜሪካ የረጅም ጊዜ አጋር ስለሆነችው ስለኢትዮጵያ ምንነት በቂ የሆነ መረጃ የሌላቸው “ናቸው ሲሉ ወርፈዋቸዋል።

የህዝብ እንደራሴው ጃሰን በማያያዝም የትራምፕ አስተዳደር ” ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ትርጉም አልባ በሆነ ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የ130 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ማእቀብን በአስቸኳይ በማንሳት የታማኝ ታዛቢነት/ ሸምጋይነት ሚና ሊጫወት ይገባል ብለዋል።

የመጀመሪያ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የምክር ቤት አባል የሆኑት የኔቫዳ ግዛት የዲሞክራት ፓርቲ የምክር ቤት አባሉ አሌክሳንደር አሰፋ የትራምፕ አስተያየትን ብስለት የጎደለው ፣ከፋፋይ እና ዲሞክራቲክነት የጎደለው አመለካከት ነው “ብለውታል። እኤአ 2018 የሪፓብሊካን ፖርቲ የቀድሞ የኮንግረስ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቴድ አለማየሁ እንዲሁ በ ፕ/ት ትራምፕ ጸረ የህዳሴው ግድብ አስተያየት ላይ የሰላ ተቃውሞ ካሰሙት እና ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ ያኖች ለሰላማዊ ሰልፍ ከዋይት ሀውስ እና ከውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ደጃፍ እንዲወጡ በማስተባበር ላይ ከሚገኙት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

 

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top