Connect with us

ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ብቻ ይማራሉ

ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ብቻ ይማራሉ
አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ብቻ ይማራሉ

ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ብቻ ይማራሉ

የመንግሥትም ሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ከጥቅምት 30 ጀምረው በቀናት ፈረቃ ሰኞ፣ ረዕቡ እና ዓርብ ሌሎቹን ደግሞ ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ ብቻ እንደሚያስተምሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። 

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እንደተናገሩት፤ ትምህርት የሚጀመረው በሁለት ዙር ነው። የመጀመሪያው ዙር የ8ኛ ክፍል የክልል ፈተና፣ የ12 ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተናን ለማካሔድ ከጥቅምት 16 ቀን እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ያለፈረቃ ሳምንቱን ሙሉ የክለሳ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል። ይህ ለፈተና እንዲዘጋጁ ያመለጣቸውን እንዲማሩ ለማድረግ ነው።

ሁለተኛው ዙር ማለትም ቀሪዎቹ ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ የሚማሩ ሲሆን፤ ይህ የሆነው ከአዋጭነት አንፃር ታይቶ መሆኑን አስረድተዋል። ቀድሞ ጠዋትና ከሰዓት በሚል ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የቀናት ፈረቃ የተሻለ ይሆናል ተብሎ ውሳኔ የተላለፈው ምልልሱን፣ መውጣት መውረዱን፣ የትራንስረፖርት ሁኔታን፣ ወጪውን እና ለወላጆች ያለውን አመቺነት ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አብራርተዋል። 

በቀሪዎቹ ቀናት ተማሪዎቹ ለብቻቸው ከንክኪ ነፃ ሆነው በቤታቸው መልመጃዎችን እና የቤት ሥራዎችን እንደሚሠሩ እንዲሁም ጥናት እንደሚያከናውኑ ታሳቢ መደረጉን ጠቅሰው፤ በፈረቃ ሲማሩ እንደየክፍሉ ስፋት በክፍል ውስጥ የሚኖራቸውን ንክኪ ለመቀነስ ቁጥራቸው ከ20 እስከ 25 ብቻ እንደሚሆኑ ገልጸዋል። 

አቶ አዲሱ እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች ተራርቀው እንዲማሩ አሁን ባሉት ክፍሎች ላይ ተጨማሪ 2ሺህ 300 ክፍሎች እንደሚያስፈልጉ ታውቋል። ሆኖም በአዲስ አበባ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በትምህርት ቤቶች ግቢም ሆነ በአካባቢያቸው በቂ ይህን ያህል ክፍሎችን የመገንቢያ ቦታ ባለመኖሩ 1ሺህ 720 ክፍሎችን በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመገንባት ዲዛይኑ ተከናውኖ፤ ውል የተገባ ሲሆን፤ ግንባታውን እስከ ጥቅምት 30 ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

የከተማ አስተዳደሩ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ቢያንስ ሁለት ሁለት የሙቀት መለኪያ በልዩ ሁኔታ በቀጥታ ግዢ እንዲከናወን ውሳኔ ያስተላለፈበት ሁኔታ መኖሩንም ገልጸው፤ ከ ጋር በመግዛት ለትምህርት ቤቶች ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል። አያይዘውም ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክፍለ ከተማ እና ከትረስት ፈንድ በማፈላለግ እያንዳንዱ ተማሪ ማስክ እንዲያገኝ ጥረት መደረጉን በመጠቆም፤ ማስኩ ለሁሉም እንደሚዳረስ አመልክተዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ዩኒፎርም መስጠት እና ምገባ ማከናወን እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ዕድሳት ላይ በመሥራት ታሪካዊ ውሳኔዎች ተላልፈዋል በማለት ያስታወሱት አቶ አዲሱ፤ ዘንድሮ ደግሞ ትምህርቱ ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ የትምህርት ጤና (school health) ፕሮግራም እንደሚተገበር ጠቁመዋል። 

በትምህርት ዘርፉ ላይ የተማሪዎች የጤና ክትትልን ለማካሄድ በካቢኔው ልዩ ውሳኔ 2ሺህ 52 በአካባቢ ጥበቃ እና በጤና ላይ የሚሠሩ ነርሶች በኮንትራት እንዲቀጠሩ በመፈቀዱ ቅጥር እየተፈፀመ ነው ብለዋል። 

ውሳኔው ጤናማ ተማሪዎች በጤናማ አካባቢ እንዲማሩ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ የከተማው አስተዳደር ከሁሉም ጉዳይ በላይ ለትምህርት ትኩረት ሰጥቶ እየደገፈ በመሆኑ ትምህርቱን እየዘመነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

( ጥቅምት 13/2013)

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top