Connect with us

ጉባዔው በሦስት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

ጉባዔው በሦስት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ
የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት

ህግና ስርዓት

ጉባዔው በሦስት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

ጉባዔው በሦስት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ሠላሳ ሰባት የባለ ጉዳይ አቤቱታዎችን በማጣራት ሠላሳ አራቱን ውሳኔ በመስጠት ሲዘጋቸው፣ ሦስት ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳቡን ልኳል፡፡

ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በማለት ጉባዔው የውሳኔ ሀሳብ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል ሁለቱ ከህጻናት መብቶች ጋር የተያያዙ ሲሆን፣ የሁለቱም ጉዳይ ወላጅ አባትን ከማወቅ መብት ጋር በተገናኘ መዝገብ ቁጥር 5287/12 እና በመዝገብ ቁጥር 2410/09 በሁለት የተለያዩ አቤቱታ አቅራቢ የተከፈቱ መዝገቦች ናቸው፡፡ 

ጉባዔው ጉዳዮቹን ከሕገ መንግሥቱና ሀገራችን ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ በስር ፍርድ ቤቶች አቤቱታ አቅራቢዎቹ ላይ የተወሰኑት ውሳኔዎች በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 36 ስር የተደነገጉ ህፃናት ወላጆቻቸውን የማወቅና የነሱን እንክብካቤ የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብትና ሌሎች ልዩ ልዩ የህጻናት መብቶችን የሚጥሱ ሆነው በማግኘቱ ጉዳዮቹ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በማለት ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳቡን ልኳል።

ሦስተኛው ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 2429/09 በአንድ ግለሰብ አቤቱታ አቅራቢነት ተከፍቶ ወደ ጉባዔው የመጣ ሲሆን፣ ጉዳዩም በግለሰቡና በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ መካከል በስር ፍርድ ቤት ክርክር ሲካሄድበት ቆይቶ በግለሰቡ ላይ በመወሰኑና ሕገ መንግሥታዊ መብቴ ተጥሷል በማለት ወደ ጉባዔው የመጣ ነው፡፡ 

ጉባዔውም ጉዳዩን ሲመረምር ከቆየ በኋላ የፍርድ ቤቶቹ ውሳኔ “የወንጀል ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሠራ ስለመሆኑ” በሚል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 22 ስር የተረጋገጡላቸውን መብቶች የጣሰ ሆኖ ስላገኘው የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳቡን ልኳል።

ጉባዔው በእለቱ ውሎ ከመረመራቸው መዝገቦች መካከልም ሠላሳ አራቱ ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ትርጉም የማያስፈልጋቸው ሆነው ስላገኛቸው ውሳኔ በመስጠት ዘግቷቸዋል፡፡(የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ፅ/ቤት)

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top