Connect with us

አለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የመንግስት ሐላፊዎችን የሚያቀራርብ ጉብኝት ተካሄደ

አለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የመንግስት ሐላፊዎችን የሚያቀራርብ ጉብኝት ተካሄደ
Ethiopian Broadcasting Corporation

አለም አቀፍ

አለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የመንግስት ሐላፊዎችን የሚያቀራርብ ጉብኝት ተካሄደ

አለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የመንግስት ሐላፊዎችን የሚያቀራርብ ጉብኝት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ትላንት ማክሰኞ 9/ 2013 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ የአለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የተለያዩ የመንግስት ሐላፊዎችን ያካተተ ጉብኝት በእንጦጦ ፓርክ አካሒዷል።

የጉብኝቱ አላማ ድንበር  ዘለል ጋዜጠኞችንና የመንግስት የመረጃ ምንጭ የሆኑ ሐላፊዎችን በማቀራረብ መንግስት መረጃን ለመስጠት በሩ ክፍት እንደሆነና ጋዜጠኞቹ በመረጃ እጥረት ምክንያት ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ እንዳያደርሱ ማድረግ መሆኑን የባለስልጣኑ መ/ቤት  ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ከተሳተፉት ቢ.ቢ.ሲ አልጀዚራ እና ኒዮርክ ታይምስን  ጨምሮ በአሜሪካ፣ በብሪታኒያ፣ በቻይና፣ በፈረንሳይ፣ ቱርክና  በማዕክላዊ ምስራቅ አገራት ለሚገኙ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚዘግቡ የሃገር ውስጥ ወኪል ጋዜጠኞች ይገኙበታል።

ከሐገር ውስጥም የመ/ቤቱን ዋና ዳይሬክተር ጨምሮ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የድርጅት ሐላፊ ቢኪላ ሁሪሳ አና ሌሎች የመንግስት ሐላፊዎች በጉብኝቱ ላይ ተገኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ተፈጥሯዊ መልክአ  ምድርን መሰረት አድርጎ የፈጠራ ችሎታና ጥበብ የታከለባቸው ስራዎችን አድንቀዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለስልጣን መ/ቤቱ የአለም አቀፉ ጋዜጠኞችን በጉብኝት መልክ  ከመንግስት ሐላፊዎች ጋር ለማቀራረብ  የሰራው ስራ አድናቆት የሚቸረው መሆኑን ገልፀው ወደፊት ተመሳሳይ ጉብኝቶችን ከመዲናው ውጪ ቢደረጉ የኢትዮጵያን ክንውኖች በሚዛናዊ እይታ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ማድረስ ያስችላል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የድርጅት ሐላፊ የሆኑት ዶ/ር ቢኪላ ሁሪሳ መንግስት ከምን ግዜም በላይ ለመረጃ ክፍት መሆኑን ጋዜጠኞቹ በማንኛውም ሰዓት መረጃ ሲፈልጉ ወደ ትክክለኛው የመረጃ ምንጭ ጋር ለማገናኘት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በፓርኩ ኪሚገኙ ባህላዊ የኩሪፍቱ ሬስቶራንት የምግብና መጠጥ ግብዣ በተካሄደበት ወቅት ጋዜጠኞችና የመንግስት ሃላፊዎች አንድ ለአንድ ውይይት  ያደረጉ ሲሆን —-ጋዜጠኞቹ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባደረገው ጥረት እንደተደሰቱና መንግስት ለመረጃ ክፍት ለመሆን ያለው ዝግጁነት በጎ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።(የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን)

 

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top