Connect with us

በአዲስ አበባ  ክፍት የሆኑ  ቤቶችንና ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የመለየት ስራ እንደሚሰራ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ክፍት የሆኑ ቤቶችንና ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የመለየት ስራ እንደሚሰራ ተገለጸ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

በአዲስ አበባ  ክፍት የሆኑ  ቤቶችንና ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የመለየት ስራ እንደሚሰራ ተገለጸ

በአዲስ አበባ  ክፍት የሆኑ  ቤቶችንና ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የመለየት ስራ እንደሚሰራ ተገለጸ

በአዲስ አበባ  ክፍት የሆኑ  ቤቶችን እና ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን በመለየት የከተማዋን የቤት ችግር በፕላን መሠረት ለመመለስ እንደሚሠራ መንግሥት አስታወቀ።

በፕላን ያልተመራ ከተማ እንዳይፈጠር ሕግ የማስከበር ሥራዎች እንደሚሰሩም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ  ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ የተሠሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እዳ ለመንግሥት ባለመመለሱ የቤት አቅርቦትን ፈጣንን ጥራት ባለው ጊዜ ለመሥራት እንቅፋት ሆኗል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በትኩረት ይሠራል  ብለዋል።

የፌዴራል ኪራይ ቤቶች ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በመሆን ተገጣጣሚ ቤቶችን እና በቶሎ ግንባታቸው የሚያልቅ ቤቶችን ለመገንባት የሄደበት መንገድ ልምድ ተወስዶ መንግሥት የአዲስ አበባ የቤት ችግርን ለመፍታት እንደ አንድ አመራጭ እንሚወስደውም አስታውቀዋል።

በአገሪቱ ያሉ ወቅታዊ ችግሮችን በመሻገር የውጭ ኩባንያዎች ጭምር በቤት ልማት ዘርፉ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሠማሩ ጥረት እንደሚደረግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። (EBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top