Connect with us

ከአማራ ክልል የተነሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ደረሰ

ከአማራ ክልል የተነሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ደረሰ
ESAT

ዜና

ከአማራ ክልል የተነሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ደረሰ

ከአማራ ክልል የተነሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ደረሰ

ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የሚሄዱ እና ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የጭነት ተሽከርካሪዎች በኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉራቻ  አሊ ዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታጣቂዎች ጥቃት ደረሰባቸው።

ከምሽቱ አምስት ሰአት ላይ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ከሚለብሰው የደንብ ልብስ ጋር የሚቀራረብ ዩኒፎርም የለበሱ ታጣቂዎች በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን እና ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎቹ እንደሚሉት የመንግስት የጸጥታ ሃይል ደንብ ልብስ የለበሱ ቢሆኑም አስቁመው ከዘረፉ  በኋላ አካባቢዉን ለቀው ተሰውረዋል ብለዋል  አሽከርካሪዎቹ ።

ከሰአታት በኋላ  የመከላከያ  ሰራዊት ወደ አካባቢው ደርሶ  አስከሪኑን አንስቷል ብለዋል።  

ጉዳት የደረሰባቸው  ደግሞ ህክምና እንዲያገኙ ሆስፒታል መግባታቸውም ተገልጿል።   

በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን ለኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ  ለአቶ ጌታቸው ባልቻ  በእጅ ስልካቸው ብንደውልም  ስልካቸው አይነሳም።(ኢሳት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top