Connect with us

የእንጦጦ ፓርካችን የእይታ ማማና የብልፅግና ጉዞአችን ወዴት?

የእንጦጦ ፓርካችን የእይታ ማማና የብልፅግና ጉዞአችን ወዴት?
Photo: Social Media

መዝናኛ

የእንጦጦ ፓርካችን የእይታ ማማና የብልፅግና ጉዞአችን ወዴት?

የእንጦጦ ፓርካችን የእይታ ማማና የብልፅግና ጉዞአችን ወዴት?

(በዶ/ር አብርሀም በላይ)

ዛሬ የመረቅነውን የእንጦጦ ፖርክን እንደ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነቴ በሌላ አውዱ ምን ማለት እንደሆነ ላካፍላችሁ!

በቅድሚያ ስለ ማለምና ስለማድረግ ቁርጠኝነትና ብቃት።

ልክ የዛሬ አንድ አመት ለህዝባችን ይጠቅማል ተብሎ የታመነበትንና የንስር አይኖች ያዮት እኛ ያልፈጠርነው ቀድሞውኑም በቦታው የኖረ አፍንጫችን ስር ያለ እጅግ ድንቅ እምቅ የከተማ ውስጥ የተረሳ ከተማና የስህበት ፈርጥ የመሆን አቅም የነበረው የእንጦጦ ጫካ የሚቀረፍፋቸው ቅጠሎችና የሚያረግፋቸው ዝንጣፊዎቹ የእናቶችና የእህቶቻችንን ጀርባ አሳዝሎ ለአመታት የተመልካች ያለህ ሲለን በአለም የምንኮራባቸውን የአትሌቲክስ ፈርጦቻችንን እያዋለደ ግዜውን በትእግስት ይጠብቅ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን የቤተመንግስት ግቢ ስራን አጠናቀቅን እንደጨረስን እንጦጦን በእይታዎቹ ራዳር አስገብቷል።

ለፕሮጀክት ጨራሽ የመጀመርያ ሰራዊቱም እይታውን አጋርቷል።

ፈረንጆች ዘ ሬስት ኢዝ ሒስትሪ ይሉታል።ከዚያ በኃላ እየሆነ ያለውን መጥታችሁ ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎችና ቴሌቭዥን ተመልከቱት።

ከቅርብ ግዜ ወዲህ በአመራሩ ዘንድ እንደ ባህል የተያዘውን ስራን በግዜውና በጥራት የመጨረስ አስፈላጊ አገራዊ አቅም የመገንባት ጅምር ሌላኛው ማሳያ ሆነ::

እንጦጦ ማማ የእይታ ማማ!!!

እነሆ እንጦጦ ፣

እጅግ ማራኪ የጤናና የታደሰ መንፈስ ገበያ

እነሆ እንጦጦ የዘመናችን ዋና የአለም ጀግኖች መካከል ከሆኑት የህክምና ሞያተኞች ኮቪድ 19ን ለሚዋጉ የአለም ብርቆች የማስታወሻ ምልክት የሰፈረበት የትውልዱ የእውቅና ሐውልት ለአገራችንና ለአለም ሞያተኞች የሰፈረበት ክቡር ቦታ።

እነሆ እንጦጦ አስታዋሽ ያጡ እናቶችና ሴት እህቶቻችን በነፃ መውጣት ሲቃ እና በበራ የነገ ተስፋ በልባቸው ፀዳል የታየበት ቅፅበት ።

በእውነት እንኳን ደስ ያለን መልካም ጅማሬ።

ወደ ዋናው የእይታ አድማሴ ልመልሳችሁ።

እንጦጦና የመፃኢ ግዜ ኢኮኖሚ ምልከታዎች።

አገራችን በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ልትወዳደርና ህዝቦችዋን ወደ ላቀ የእድገት ደረጃ ለማሳተፍ የወደደች ከሆነ የውድድሩን አውድ ለመመልከት ሌላ የላቀ እይታን ይጠይቃታል። ከፍ ያለ እይታ።

የአለማችን ኢኮኖሚ መልኩ እጅግ አየተቀየረ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚፈጠረው ሀብት በፍጥነት አያደገ እና በአለም የሐብት ባለቤትነት ሰንጠረዥ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠር እድሜ ካላቸው ኩባንያዎች ቀድመው ከላይ የሚጠሩት ሀብታም ኩባንያዎች የቴክ ኩባንያዎች ናቸው። የመሬት የጉልበት የመረጃ ሐብቶች የኢኮኖሚ ምንጭነት በግዜ ውስጥ በሌላ ተወዳዳሪ ሀብት እየተካ በመምጣቱ ጉዳይ ቀደም ሲል የጠቀስኩትን የቀደሙና የአሁን ዘመን ኩባንያዎችን የሐብት መጠንና ደረጃ በፍጥነት እየቀየረ ያለው ሀቅ ነው።

ይህ የትኩረት ኢኮኖሚ(attention economy)በምድር ላይ ያሉ ወይም ግኡዝ የማይዳሰሱ የትኩረት ጉዳዮችን ወደ ዲጂታል አውድ በማፍሰስ የሰዎችን እጅግ በጣም ውድ እና ያጠረ ሐብት(scarce resource:attention )የማቋቋም እሽቅድምድም ነው።

የእንጦጦንም ሆነ ሌሎች መሰል ስራዎቻችንን የምናይበት እይታ የተለየ ነው የምንለው ለዚህ ነውና

እኛ እንደ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር አገራችንን ዲጂታል ኢትዮጰያ 2025 በሚል ስትራተጂ ከከተማ ወጥተን ህዝባችን ወደሚገኝበት ገጠር ለመሔድ በሩቅ አልመናል።

በብሔራዊ ቤተመንግስት በሸገርና በእንጦጦ ፓርኮች አሁንም በጀመርናቸው ጎርጎራ ወንጪና ኮይሻ ያየናቸውና የምንፈፅማቸው ስራዎች በአይን ከሚታየውና በእጅ ከሚዳሰሰው ነገር በላይ የመፃኢው የኢኮኖሚ አለም የሚጠይቀውን መስፈርት ይዞ በአለም ተወዳዳሪ ለመሆን የሚደረገውን እጅግ ፈጣን ጉዞ በማሟቅ ውጀምረናል።

የኘሮጀክቱ ምረቃ አስተባባሪዎች በፕሮግራሙ ሩጫን ያካተቱት ይህ ታይቷቸው ሳይሆን አይቀርም። እኔም ቀላል አይደለሁም ሶስተኛ ነው የወጣሁት።

ገና ገና ብዙ መሮጥ ይኖርብናል ወገኖቼ በርቱ ተያይዘን በፍቅር እንሩጥ በርቱ።

የዲጂታል ኢኮኖሚ እይታ

#የእንጦጦ ፓርክ ማማ

ብልፅግና የከፍታ እይታ ነው#

ሰናይ የሳምንት መጨረሻ።

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top