Connect with us

የኮሮና ቫይረስ እና ሕፃናት

የኮሮና ቫይረስ እና ሕፃናት
A child helps a friend put on a face mask as a precaution against coronavirus. Photograph: Anadolu Agency/Getty Images

ጤና

የኮሮና ቫይረስ እና ሕፃናት

የኮሮና ቫይረስ እና ሕፃናት

በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት 69 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከጥቂት ሳምነታት በፊት የተገኘው መረጃ አንዳሚያሳየው 644 የሚሆኑት ከ 0 እስከ 4 አመት ያሉ ሕፃናት ሲሆኑ 788 ያህሉ ደግሞ ከ 5 እስከ 14 አመት ያሉ ሕፃናት ልጆች ናቸው፡፡ህፃናት ልጆችም በኮሮና ቫይረስ ተይዘው እንደ አዋቂውች ምንም የህመም ስሜቶች ወይም ቀላል የህመም ስሜቶች ሊያጋጥማቸው ሲችል ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የመግባታቸው እድል ግን ዝቅ ያለ ነው፡፡

ቫይረስ ከጨቅላ ህፃናት ጀምሮ የሚይዝ በሽታ ሲሆን ህፃናቱ ምንም አይነት የህመም ምልክት ላያሳዩ ወይም ቀለል ያለ የህመም ምልክቶች ሊኖራቸው ቢችልም ወደ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል ግን ቫይረሱን ያስተላልፋሉ፡፡ ህፃናት ልጆች በሽታን የመከላከል አቅማቸውን ለማጎልበት ቤተሰቦች አቅማቸው በሚችለው መጠን ለልጆቻቸው የተመጣጠነ ምግብ ቢመግቡ ተመራጭ ነው፡፡
የተለየ የህመም ስሜት እንደ ሳል ትኩሳት፣የአየር/ማጠር፣ቶሎቶሎ የመተንፈስ እና ሌሎች የበሽታ ምልክቶች ካየንባቸው ወደ ጤና ተቋማት መውሰድ እና አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ልብ ይበሉ! የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በምናደርገው ጥንቃቄ ለልጆቻችን የሚያስፈልጉ የህክምና ክትትሎችን መዘንጋት ተጨማሪ የጤና እክል እንደሚያስከትሉ አንዘንጋ፡፡ስለሆነም ህፃናት በቂ የቀጥታ የፀሀይ ብርሀን እንዲያገኙ ማድረግ ፣ የእናት ጡት ወተት እስከ 2 አመት ድረስ (ከ6 ወር በኃላ ከተጨማሪ ምግብ ጋር) መመገብ እንዲሁም የክትባት ጊዜያቸውን በጠበቀ መልኩ እና በተለያየ ጊዜ ለተላላፊ በሽታዎች ማስከተብ የሚኖርብንን ክትባት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

በዚህ ወቅት ግዴታ ሆኖ ህፃናት ልጆቻችንን ይዘን ከቤት ከወጣን ከሁለት አመት በላይ ለሆኑ ህፃናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያወልቁ፣የእጃቸውን ንፅህና እየጠበቅን ርቀታቸውን በመጠበቅ ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ባለመሆን ራሳችንን እና ልጆቻችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ(ቅዱስ ጳውሎስ ሆ/ል ሚልኒየም ሜዲካል ኮሌጅ)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top