Connect with us

መስከረም ጠብቶም ሞት – ብራ ኾኖም ጨለማ

መስከረም ጠብቶም ሞት፡፡ ብራ ኾኖም ጨለማ፡፡
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

መስከረም ጠብቶም ሞት – ብራ ኾኖም ጨለማ

መስከረም ጠብቶም ሞት፡፡ ብራ ኾኖም ጨለማ፡፡
አሁን ማልቀስ ለወገን ሳይኾን ለራስ ነው፡፡
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

መስከረም ጠብቶም ሞት መሪር ነው፡፡ ጨለማውን አለፍኩ ሲሉ በድቅድቅ መዋጥ ይከብዳል፡፡ እንኳን ሰው አውሬ ይሄን ያደርጋል ብሎ መጠበቅ አይቻለም፡፡ ይህ በጦር ግንባር የተፈጸመ ጀብድ አይደለም፡፡ በእናት ሆድ ላይ የተደረገ ክፉ ስራ እንጂ፤

ጨለማውን አለፍን ብለን ስለ ብራ መኾን ስናስብ ወገን ላይ ዳግም ጨለማ ተኛ፡፡ በመተከል እንዲህ አይነቱ ተግባር እንግዳ አይደለም፤ ከትናንቱ እየከፋ ዛሬ የደረሰ ሰቆቃ ነው፡፡ ይሄ ኢትዮጵያ ላይ መፈጸሙ ሳይሆን ሰው ነኝ ብሎ የሚያስብ ሁሉ በወል ስም ስለሚጠራ ሰውን ሁሉ የሚያሸማቅቅ ነው፡፡

እስከመቼ የሚለውን የሚመልስ ማንም የለም፡፡ ወቅት እየጠበቀ ግን ሰበር ዜና ይሆናል፡፡ ከፈጸሙት በላይ ግብር እየበሉ ሀገር መጠበቅ ያቃታቸው ሹማምንት ምን ያህል ህዝቡን እንደጠሉት ማሳያ ነው፡፡ በየቀኑ የሞት ዜና ቢሰማም የአዳራሹን ድግስ እንኳን አላደበዘዘውም፤ ዝርክርክና ተራ አጀንዳዎች ከፍ ሲሉ ህግና ፍትህ ቦታቸውን ለቀዋል፡፡ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ምክንያት በሚፈበርኩ አረመኔዎች የእናት ሆድ የምታርድ ቤተሰብ የምትፈጅ ዘር ተለይቶ የሚጠቃባት ሲዖል ሆናለች፡፡

ዲሞክራሲያዊ አፈናዎች የለመድናቸው ናቸው፡፡ መንግስታዊ ስቆቃም ምክንያት እየተሰጠው ሲደረግ ኖሯል፡፡ ሰባና ሰማኒያ አመት ከለመድነው ተግባር ያፈነገጠው ጎጆዋ ውስጥ ያለች እናት በማታውቀው ጉዳይ መታረዷ ነው፡፡

ሞት አልባ መፈናቀልን ስንኮንን በራስ ጎጆ ወደ መታረድ አድጎ የመጣው በጥቂት አመት ነው፡፡ ለምን ብሎ ለመጠየቅ ማንን እስከማለት የደረስን መከታ አልባ ዜጎች ሆነናል፡፡ እናም ብራው ጨለመብን፣ መስከረሙ ጎርፍ ሆነ፤ ምድር አደይ ለብሳ እኛ ለማቅ ተመረጥን፡፡

አሁን ወገኔ እንዲህ ሆነ ብሎ ማልቀስ ወቅቱ አይደለም፡፡ አሁን ማልቀስ ለራስ ነው፡፡ እንደ እየሩሳሌም ሴቶች ለራሳችሁ አልቅሱ ብሎ የሚመክረን መሲህ አጥተን እንጂ እያንዳንዱ ዜጋ መታረድ መጀመሩ ይሰማኛል፡፡

ጥፋት የሌለበት ወገን ሞት ሲነገር ለቅሶው ለሟች ሳይሆን ለራስ ነው፡፡ በደሉ፣ ሞቱና ስቆቃው ራሳችን ደጃፍ ደርሷል፡፡ ወዮ ለኔ ማለት አሁን ነው፡፡ እሱም ማልቀስን መፍትሔ ካደረግነው፡፡ እስቲ ከእንባችን ማዶ ያለውን የነጻነት መንገድ እንመልከተው፤ እሱ ምናልባት የሳቅ መፍትሔ ይሆን ይሆናል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top