Connect with us

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የስጦታ ማረጋገጥ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠ

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የስጦታ ማረጋገጥ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የስጦታ ማረጋገጥ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠ

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የስጦታ ማረጋገጥ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠ

– ማንኛውም ሽያጭ እና ግዢ እንዲሁም ብድር ከባንክ የሂሳብ የተዘዋወረበት ማረጋገጫ ካልቀረበ አይረጋገጥም፣

~ በአጭሩ በጥሬ ገንዘብ የሚከናወን ግዥና ሽያጭን ከልክሏል፣

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ጥሬ ገንዘብን ሥርዓት ለማስያዝ ሲባል መንግስት የተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑ የሚታወቅ መሆኑን አስታውሶ፤ ህገወጥነትን ለመከላከል እና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ሲባል ከዛሬ መስከረም 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ኤጀንሲው ባደረገው የአሰራር ማሻሻያ መሰረት የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ተገልጋዮች የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፡-

በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፣

• በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት ሲል አስታውቋል።

በመሆኑም የሽያጩ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ ክፍያው ከላይ በተገለጸው አግባብ የተፈጸመ ስለመሆኑ የሚገልጽና በባንኩ ማህተም የተደገፈ የሂሳብ ማስተላለፊያ (#Bank Transfer Slip) የሰነድ ማስረጃ መቅረብ አለበት ብሏል።

በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል ሌሎች የአሰራር ማሻሻያዎች እስኪደረጉ ድረስ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ኤጀንሲው ላልተወሰነ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው ያወጣው መግለጫ ያብራራል፡፡(CAPITAL)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top