Connect with us

“የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት ከመሪዎች በላይ ነው” አቶ ሽመልስ አብዲሳ

“የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት ከመሪዎች በላይ ነው” አቶ ሽመልስ አብዲሳ
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

“የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት ከመሪዎች በላይ ነው” አቶ ሽመልስ አብዲሳ

በአማራ ክልል ሰላም እንዲከበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በትላንትናው ዕለት በባህርዳር ከተማ እውቅና ተሰጥቷል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮምያ ክልል ኘረዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ካደረጉት ንግግር ተከታዩ ይጠቀሳል።

~ የአማራንና ኦሮሞን ህዝቦች ለዘመናት የዘለቀ ወንድማማችነትና አንድነትን በማጠናከር የኢትዮጵያ ብልፅግና እንዲሳካ በትብብር ሊሰሩ ይገባል፣

~ የአማራና ኦሮሞ ግንኙነት ረጅም ታሪክ ያለውና በማንኛውም መንገድ ሊለያይ የማይችሉ ህዝቦች ናቸው።

~ የሁለቱ ህዝቦች አንድነት የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፈንታ በመወሰንና አንድነቷ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጎላ ሚና አለው፣

~ ለውጡ ኢትዮጵያን ከአደጋ በማውጣት አስቀጥሏል። በቀጣይም ይህው ለውጥ የሃገሪቱን ብልፅግና እንዲያረጋግጥ ብስለት ያለው አመራር ያስፈልጋል፣

-~ ኢትዮጵያ በእኩልነትና ወንድማማችነት የተመሰረተች ጠንካራ ሃገር ነች። ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የህዝቦች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በጋራ መስራት ይገባል፣

~ የሃገርን ብልፅግና ለማረጋገጥም ያለፈውን በይቅርታ መሻገር ይገባል። ለዚህም ትንንሽ ጉዳዮች ወደ ጎን በመተው ሃገርን ሊያሻግሩ በሚችሉ በታላላቅ ጉዳዮች ላይ አበክሮ መንቀሳቀስ ይገባል፣

~ “ባለፉት ጊዜያት የህዝቦችን አንድነት የሚሸረሽሩ በርካታ አሜካላ እሾህ የሆኑ ዘሮች ተዘርተዋል። እነዚህ የሃገር ፀር የሆኑ እንቅፋቶችን ለቅሞ ለመጨረስ ጊዜ የሚወስድና በሆደ ሰፊነት ተጋግዞ መስራት ያስፈልጋል፣

~ የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት ከመሪዎች በላይ ነው።(ኢኘድ)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top